በግዛት ድራማ ላይ ነገሮች ከቀን ወደ ቀን እየተለዋወጡ እና ይበልጥ አጓጊ እየሆኑ መጥተዋል። በዚህ ወር የታዩት ታላላቅ ክስተቶች እና የገጸ ባህሪያቱ ፍጥጫ ድራማውን ወደ አጓጊ ውጥረት አሸጋግረውታል።
ያቺ ወሳኝ ሚሞሪ ካርድ የት ትገኝ ይሆን?
በሀረግ እና በሰላም መካከል ያለው ፍጥጫ አሁን ላይ ጣሪያ ነክቷል። ሰላም (የቤት ሰራተኛዋ እና የተፈሪ የልጁ እናት) ከመርማሪ ተሾመ ጋር በመተባበር ሀረግን በቁጥጥር ስር ለማዋል አደገኛ እርምጃ ወስዳለች።
ሰላም ሀረግን አስቆጥታ ወንጀሏን እንድታምን በማድረግ በድምፅ መቅጃ ስትቀርጻት የነበረው ትዕይንት እጅግ አስደንጋጭ ነበር። ሀረግ ሰላምን አንቃ በያዘችበት ወቅት ሰላም በድምፅ መቅጃው የሀረግን የኑዛዜ ቃል መቅዳት ችላለች። ሰላም አምልጣ ተሾመ ጋር ብትደርስም፣ ትልቁ ችግር ግን የድምፅ መቅጃው ሚሞሪ ካርድ በሰላም እጅ አለመገኘቱ ነው! አሁን ቤተሰቡ እና በቤቱ ውስጥ ያሉት የቤት ሰራተኞች በሚሞሪ ካርዱ መገኛ ምክኛት ታውከዋል። በሌላ በኩል ሀረግ በዚህ ሁኔታ ተበሳጭታ የት እንደገባች ሳይታወቅ ጠፍታለች።
የኪያ ዳግም ወደ ሱስ መመለስ
የኪያ ሁኔታ ለተመልካች ልብ ሰባሪ ሆኗል። ለተወሰነ ጊዜ ከሱስ ርቃ የነበረ ቢሆንም፣ የሞተው አባቷ ተፈሪ ናፍቆት እና የሚያዳምጣት ሰው ማጣቷ ክፉኛ ጎድቷታል። ኪያ ስሜቷን የምታካፍለው ሰው ስትፈልግ ቤተሰቦቿ ችላ ማለታቸው ለበለጠ ብስጭት ዳረጋት።
በዚህም ምክንያት ወደ ሰመረ የቀድሞ ፍቅረኛ ሊዲያ ጋር በመሄድ ስሜቷን ለማርገብ ስትሞክር ዳግም ከዕፅ ጋር ተገናኝታ በሱስ ተሸነፈች። አሁን ላይ በሱስ ተዘፍቃ በሰራችው ነገር ከፍተኛ የፀፀት እና የጭንቀት ስሜት ውስጥ ትገኛለች።
የኑሀሚን እና የበረከት ፍቅር ይሳካ ይሆን?
ኑሀሚን አሁንም ቢሆን የፍቅር ህይወቷ አልሰመረላትም። ከአሮን ጋር የነበራት ግንኙነት መበላሸቱ እና እሱ ተመልሶ ይቅርታ መጠየቁ ስሜቷን አላረጋጋውም። በተጨማሪም አባቷ ሰላምን ወደ ቤት ይዞ መምጣቱ ለኑሀሚን ትልቅ ቅሬታ ሆኖባታል።
በነዚህ ሁሉ ውጥረቶች ምክንያት፣ ኑሀሚን አዲስ ለቀረባት እና ፍላጎቱን ለገለጸላት በረከት ዕድል ለመስጠት ተቸግራለች። በረከት ኑሀሚን እንድትቀርበው ቢፈልግም፣ የሷ ልብ ግን አሁንም በቤተሰቧ እና ባለፈው ህይወቷ የተነሳ በጥርጣሬ ተሞልቷል።
በቀጣይ ምን የሚፈጠር ይመስላችኋል? ሚሞሪ ካርዱ መቼ ይገኝ ይሆን? ሀረግስ የት ሄዳ ይሆን?
#ግዛት ዘወትር ከሰኞ - ረቡዕ ከምሽቱ 2:30 በ #አቦልቲቪ፣ ዲኤስቲቪ ቻናል 465 እንዳያመልጥዎ!
በ #MyDStv አፕ አሁን አገልግሎቱን ያስቀጥሉ: https://mydstv-thiane.onelink.me/ivCe/qpuy2sa6 እና በ DStv Stream App የሚወዱትን የአቦል ቲቪ ድራማዎች ይመልከቱ፡ http://tinyurl.com/bdh2j9ed



