አቦል ቲቪ መዝናኛዎች በዚህም ወር ተመልካቾችን ቀልብ መግዛታቸውን ቀጥለዋል! ከልብ ሰባሪ ስንብቶች እስከ አስደሳች ጉብኝቶች፣ እንዲሁም አዳዲስ የፍቅር ሽኩቻዎች ድረስ በዚህ ወር የቴሌቪዥን መስኮታችንን በጉጉት እንድንጠባበቅ ያደረጉን አራት ዋና ዋና ክንውኖችን እነሆ፦
1. "ባሻገር"፡ ያልተጠበቀ የምዕራፍ አንድ ማጠቃለያ
2. "Out N' About"፡ የአዲስ አበባ ድንቅ ገጽታዎችና ጣፋጭ ምግቦች
ከ"Out N' About" ጋር በዚህ ወር አዲስ አበባን በአዲስ መነፅር አስመልክቶናል። በከተማዋ የጎልፍ መጫወቻ ሜዳ ጎልፍ ከለብ ያደረግነውን አስደሳች ቆይታ ተከትሎ፣ ከተለያዩ ባህሎች የተውጣጡ አስደናቂ ምግቦችን ቀምሰናል። የአዲስ አበባ የባህል ብዝሃነት በምግብ ጠረጴዛ ላይ ሲቀርብ ማየት ለተመልካቾች ልዩ ጣዕም የሰጠ ቆይታ ነበር።
3. "ግዛት"፡ የሐረግ እና የሰላም የሞት ሽረት ፍጥጫ
በ"ግዛት" ድራማ ውስጥ በሐረግ እና በሰላም መካከል ያለው ጦርነት ተጋግሏል። ሰላም ከመርማሪ ተሾመ ጋር በሚስጥር በመተባበር፣ ሐረግን ከስልጣን ለማውረድና በእስር ለመቅጣት የሚያስችላትን መረጃ ለማሰባሰብ የምታደርገው ጥረት ታሪኩን ከፍተኛ ውጥረት ውስጥ ከቶታል። ሃረግ ይህን የድብቅ ሴራ የደረሰችበት ይመስላል።
4. "ደጋምባ"፡ የፍቅር ሦስት ማዕዘን እና የልጅ ፍላጎት
አዲሱ ድራማ "ደጋምባ" ገና ከጅምሩ ተመልካቾችን እያስገረመ ይገኛል። በምሥራቅ፣ በሰውመሆን እና በሰውመሆን የቀድሞ ፍቅረኛ ፍካት መካከል ያለው የፍቅር ሽኩቻ እየተፋፋመ ነው። በተለይ ልጅ ለመውለድ ማንኛውንም መስዋዕትነት ለመክፈል የተዘጋጀችው ምሥራቅ፣ ልጅ ያሰጣል የተባለውን ሚስጥራዊ ዕፅዋት ለመሞከር መወሰኗ እና የፍካት ጣልቃ ገብነት የታሪኩን ሙቀት ጨምሮታል።
የአቦል ቲቪ ፕሮግራሞች በየሳምንቱ አዳዲስ ድንቆችን ይዘው ይቀጥላሉ! እንዳያመልጣችሁ!
በ #MyDStv አፕ አሁን አገልግሎቱን ያስቀጥሉ: https://mydstv-thiane.onelink.me/ivCe/qpuy2sa6 እና በ DStv Stream App የሚወዱትን የአቦል ቲቪ ድራማዎች ይመልከቱ፡ tinyurl.com/bdh2j9e


