channel logo
Bashager Home Page Billboard
channel logo

Bashager

465DramaPG13

የበሻገር ፍትህ ፍጥጫ! የመጀመሪያው ምዕራፍ አስገራሚ ማጠቃለያ

ዜና23 ዲሴምበር 2025
የ"በሻገር" ምዕራፍ 1 ባለፈው ሳምንት መጠናቀቁን ተከትሎ፣ ተመልካቾች በተፈእጠሩት አስደናቂ ሁኔታዎች ተገርመዋል። በሴራ፣ በናፍቆት እና ባልተጠበቁ ክስተቶች የታጀበው የፍጻሜው ክፍል፣ ለሁለተኛው ምዕራፍ በርካታ ጥያቄዎችን ጥሎ አልፏል።
Bashager Article cover

የ"በሻገር" ምዕራፍ 1 ባለፈው ሳምንት መጠናቀቁን ተከትሎ፣ ተመልካቾች በተፈጠሩት አስደናቂ ሁኔታዎች ተገርመዋል። በሴራ፣ በናፍቆት እና ባልተጠበቁ ክስተቶች የታጀበው የፍጻሜው ክፍል፣ ለሁለተኛው ምዕራፍ በርካታ ጥያቄዎችን ጥሎ አልፏል።

የተደበቀው ሚስጥር ይፋ ሆነ

የአካ ቦቹ ባለቤት ኒሻን ልጇን ፍለጋ ከአረብ ሀገር ተመልሳለች። ከ8 አመታት በፊት ልጇን በቤተክርስቲያን ውስጥ ጥላ ስትሄድ የተረከበቻት ሴት ማን እንደሆነች አሁን አውቀናል። እሷም ሌላ ማንም ሳትሆን የክፉው አበጀ ባለቤት፣ ጠንካራዋ ጠበቃ ሚዛን ነች። የሚገርመው ደግሞ ሚዛን የአካ ቦቹን ጉዳይ ስትመረምር የነበረችው የኢንስፔክተር ምስክር የቅርብ ጓደኛ መሆኗ ነው።

የእውነት መገጋጠሚያ

ኒሻን ልጇን በሚዛን እጅ በመተውዋ ይቅርታ ስትጠይቅ፣ በአጋጣሚ የመጣችው ኢንስፔክተር ምስክር ስለ አካ ቦቹ ሁኔታ ትናገራለች። ኢንስፔክተሯ አካ ቦቹ በእስር ላይ ሆኖ ስለ ሚስቱ የነገራትን ታሪክ እና የኒሻንን የህይወት ታሪክ በማገናኘት፣ ሁለቱ ተፈላላጊዎች ባል እና ሚስት መሆናቸውን አረጋገጠች። ይህ አጋጣሚ ለታሪኩ ትልቅ መለወጫ ነጥብ ሆኗል።

በናፍቆት የታጀበው መገናኘት

ምንም እንኳን የፖሊስ ጣቢያው የበላይ መርማሪ ከአበጀ እና ከኩራባቸዉ ጋር በመመሳጠር አካ ላይ ለማስፈረድ ቢሞክርም፣ ኢንስፔክተር ምስክር ግን በድፍረት አካ እና ኒሻን በምስጢር እንዲገናኙ አድርጋለች።

የአካ እና የኒሻን ዳግም መገናኘት ልብ የሚነካ ነበር። አካ በችግሩ ወቅት ጥሏት በመሄዱ በታላቅ ፀፀት ይቅርታ ጠይቋት ተላቀሩ። ጠበቃ ሚዛንም የአካ ቦቹን ነጻነት ለማስከበር በችሎት ፊት ለመቆም ወሰነች።

የአበጀ ድንጋጤ እና የመጨረሻው ልብ አንጠልጣይ ትይንት

የሙስናው ተባባሪ የሆነው የፖሊስ አለቃ፣ አካ እና ኒሻን መገናኘታቸውን ለአበጀ እና ለኩራባቸዉ ይነግራቸዋል። ጉዳዩ ወደ ፍርድ ቤት ማምራቱ እና በጠንካራ ጠበቃ መወከሉ ክፉዎቹን አስደንግጧቸዋል።

"ማናት ይቺ ጠበቃ?" ብለው የጠየቁት አበጀ እና ኩራባቸው፣ መልሱ "ሚዛን" መሆኑን ሲሰሙ አበጀ በከፍተኛ ድንጋጤ ከመቀመጫው ተነስቷል። የራሱ ሚስት የእርሱን ሴራ ልታጋልጥ መቆሟ ምዕራፍ 1 በትልቅ ጉጉት እንዲጠናቀቅ አድርጓል።

ሚዛን የባለቤቷን እውነተኛ ማንነት ስታውቅ ምን ታደርጋለች? አካ ቦቹ ንፁህነቱን አረጋግጦ ቤተሰቡን ዳግም ይሰበስባል?

ኩራባቸዉ እና አበጀ ከገቡበት አረንቋ እንዴት ይወጣሉ? አሁንም በባሻገር መመለስ መመለስ ያለባቸው ጥያቄዎች ሆነዋል!

የአቦል ድራማዎች እንዳያመልጥዎ ደምበኝነትዎን ያስቀጥሉ፡ https://mydstv-thiane.onelink.me/ivCe/qpuy2sa6