channel logo
Gizat S1

አዲስ አገዛዝ በግዛት፡ አሮን የቤተሰቡን ሕገወጥ ግዛት መምራት ሲጀምር!

ዜና09 ኖቬምበር 2025
የግዛት ድራማ ባለፉት ሳምንታት አስገራሚ የመሪነት ሽግግር ታይቶበታል። የቤተሰቡ የወንጀል ግዛት መሪነት ያልተጠበቀ ሰው እጅ ገብቷል፣ የሐረግ ልጅ አሮን!
Gizat S1 article

የግዛት ድራማ ባለፉት ሳምንታት አስገራሚ የመሪነት ሽግግር ታይቶበታል። የተፈሪ ቤተሰብ የወንጀል ግዛት መሪነት ያልተጠበቀ ሰው እጅ ገብቷል፣ የሐረግ ልጅ አሮን! 

የአሮን ትልቁ ክህደት

አሮን ወደዚህ ቦታ ለመድረስ ትልቅ መስዋዕትነት ከፍሏል፤ እሱም  የሚወዳቸውን እና የሚያምኑትን ሰዎች መክዳት ነበር። እናቱን ሐረግን ከእስር ለማስለቀቅ ሲል፣ ከመርመራሪ ተሾመ እና ከፍቅረኛው ኑሃሚን ጋር የነበረውን ግንኙነት እንደ መሳሪያ ተጠቀመበት። አሮን፣ የእናቱን ነጻነት የሚያረጋግጥ አስፈላጊ መረጃ ለማግኘት ሲል፣ ኑሃሚንን እና አባቷን አታለለ። ከኑሃሚን ጋር ያሰበውን ሰርግ ሰረዘ። ይህ ድርጊት አሮን ከዚህ በፊት ከነበረው ለስላሳ ባህሪ ሙሉ ለሙሉ የተለየ ሰው መሆኑን የሚያሳይ ነበር።

የሐረግ ምርጫ፡ አሮን እንዴት ተመረጠ?

ሐረግ ከእስር ከተፈታች በኋላ፣ ለስራ ከሀገር ውጭ ልትወጣ ስትል ፣ የቤተሰቡን መሪነት የሚረክብ ብቸኛ ሰው መምረጥ ነበረባት። ብዙዎች ሰመረ የመምራት ዕድሉ ሰፊ ነው ብለው ሲጠብቁ፣ ሐረግ ያልተጠበቀ ውሳኔ አሳልፋለች፡ ቤተሰቡን እንዲመራ የመረጠችው አሮንን ነበር!

የአመራር ጉዞው አጀማመር

መጀመሪያ ላይ፣ አሮን ይህን ከባድ ኃላፊነት ለመሸከም  አመንትቶ ነበር። በኋላ ግን ቤተሰቡን ለመምራት ወሰነ። አሮን ቀስ በቀስ የአመራር ልጓሙን በመያዝ ከቤተሰቡ አጋሮች ጋር መሥራት እና ጠላቶቻቸውን መቋቋም ጀመረ። ይህ ጉዞ ለሱ አዲስ ቢሆንም፣ አሮን ቀስ በቀስ የንግዱን ውስብስብነት እየተማረ፣ ትዕዛዝ መስጠትና መወሰን ጀመረ።

የውስጥ ተቃውሞዎች እና ሴራዎች

የአሮን ወደ ስልጣን መምጣት ግን የሁሉም ሰው ደስታ አልነበረም! ከቤተሰቡ ውስጥ ከባድ ተቃውሞ ገጥሞታል። ዋና ተቃዋሚዎቹ አጎቱ ምትኩ እና የሰመረ ሚስት ሊዲያ ነበሩ።

ሊዲያ እና ምትኩ ሰመረ ለቤተሰቡ ንግድ እና ሚስጥሮች የበለጠ ልምድ ያለው መሪ ነው ብለው ስለሚያምኑ ፣ አሮንን ከሥልጣን ለማውረድ እና ሰመረን በቦታው ለመተካት ሴራ መጎንጎን ጀምረዋል። አሮን አሁን ከውጭ ከሚመጡ ጠላቶች በተጨማሪ፣ ከቤተሰቡ ውስጥ የሚመጡ የቅርብ ስጋቶችን መጋፈጥ ይኖርበታል!

ቀጥሎስ ምን ይሆናል? አሮን በታማኝነቱ የከፈለውን ዋጋ ተቀብሎ፣ ስልጣኑን ለማስጠበቅ እና ከውስጥም ከውጭም ያሉትን ሴራዎች ለመቋቋም የሚችለው እንዴት ነው? በቀጣይ የግዛት ክፍሎች እንጠብቅ!

#ግዛት ዘወትር ከሰኞ - ረቡዕ ከምሽቱ 2:30 በ #አቦልቲቪ፣ ዲኤስቲቪ ቻናል 465 እንዳያመልጥዎ!
በ #MyDStv አፕ አሁን አገልግሎቱን ያስቀጥሉ: https://mydstv-thiane.onelink.me/ivCe/qpuy2sa6 እና በ DStv Stream App የሚወዱትን የአቦል ቲቪ ድራማዎች ይመልከቱ፡ http://tinyurl.com/bdh2j9ed