እነሆ በዕፀህይወት ድራማ የሰብለ ተንኮል ፣ የአሸናፊ ክህደት በሁለት መለያ መጫወቱ ወዳጅም ጠላትም መሆን መቻሉ የዕፀህይወትን ህልውና ከባድ የምድር ሲኦል ወደ መሆን አድርሷል ለሃብት ብለው የተፈጥሮ ወራሽ የሆነችውን ዕፀህይወት ለመግደል በማሴር የመጨረሻ እፎይታ ለማግኘት በጥረት ላይ መሆናቸው እነ ሰብለ ሳይሳካ ቀርቷል ።
ዕፀህይወትም ቢሆን ሞት ተደግሶላት ከዚህ የሞት ወጥመድ ማምለጥ ችላለች የእጅ ሽጉጥ ተተኩሶባት ቆዩ ያላት ነብሰ ይሉ በተአምር መትረፍ ችላለች ።
የውስጥ ሰላም ፣ ፍቅር ፣ ደስታ ፣ መተማመን መስዋዕትነት መልክ መልክ ይዘው በየ ረድፉ ተሰልፈው በድንቅ ይዘት የሚታዩበት ዕፀህይወት ድራማ በአስገራሚ የታሪክ ክስተት ታጅቦ የታሪኩ አስኳል የሃሳብ ጥልቀት የመነሻ ጅምር ዕፀህይወትን ለመቅጠፍ በር ላይ ነው የሚገኘው ።
እነ ሰብለ አንዲት ነብሰ ሰላም አሳጥታ የቀን ቅጀት ሆኖ የምድር ሃሳብ የሃብት መቀራመት ውጥን የማህል መንገድ ድንጋይ ሆናባቸ ያለችን ምስኪን የሚያሳሳ ነብስ ያላትን ዕፀህይወት ለመቅጠፍ በሃይል ተነስተዋል ።
ቀደም ሲል እነ ሰብለ በስውር ማንም በማይረዳበት መልኩ የዕፀህይወት ቤተሰብ መኖሪያ ቤትን አውድመው አዛኝ ሆነው ለጥየቃ መተዋል ዛሬ ደሞ በግልጽ በሚመስል የጠለፋ ድራማ ውድ ነብስ ለመገበር ተንኮል ሸርበው ነበር ግን መሳካት አልቻለም ግን ይህን ያህል ለምን ለገንዘብ ፣ ለስልጣን ወይስ የክፋት ባለሟሎች ሆነው ይሆን ድራማው መልስ አለው ።
ለብቻው ከጀርባዋ የሚከወን ሁሉ የክፋት ግብርን ከደግ ነብሷ ጋር በስውር የሚመክት ልብ ያላት ዕፀህይወት ፈተናው ቢፀናም የሃሳብ ልክ የደግነት ማሳያ ናት እና ጠላት ማሸነፍ አልቻለም ።
የአባቷ ውርስ ከሌላ በሚወለድ ሰጋ ወንድም ፣ የህግ እናት አይገባትም በሚል በወንድሟ አጉል ፍላጎት ፈተና ውስጥ የገባችው ዕፀህይወት ፣ የእስክንድር እና እናቱ ሰብለ የውስጥ ክፋት የልጁ ስልጣን መጠማት በታሪክ መስዋዕትነት የተከፈለበትን ድርጅትን በችኮላ ልምድ በሌለው አእምሮ በመፈለግ ብቻ ለመምራት የሚመኘው እስክንድር በክፋት ሆኖ የዕፀህይወት እናት ቤት የሚባለውን የገጠር ቤት በእሳት አውድመው ሊሳካለት ያልቻለው የነ ሰብለ ቡድን ዛሬ ፊት ለፊት መከሰት ጀምሮአል ይህ ሃሳብ ይሰምር ይሆን ድራማው መልስ አለው ።