ሃብት የህይወት ደስታ ወይስ የሰቀቀን ቀናት ምንጭ ፦ ዕፀህይወት ድራማ ፣
የምድርን የሰው ልጅ ፈተና በማራኪ የታሪክ ፍሰት በልኩ የሚተርከው ዕፀህይወት ድራማ በመቼት ፣ ግጥምጥሞሽ ታጅቦ ወደ አዲስ ውስብስብ የትዕይንተ ምዕራፍ በመሸጋገር ላይ ነው ።
የዕፀህይወት ደጋፊዎች የሃሳብ የሞራል ፣ አማካሪ መመኪያዎች በሞት ሲለዩ ለብቻዋ መቅረቷ በተቃራኒ የቆሙ የሃብት ተፋላሚዎች በአገኘውሽ ስሜት በደስታ ሆነው የተንኮል ሴራ በመሸረብ ላይ ናቸው።
ዕፀህይወት በውርስ የተገባትን ሃብት ለመንጠቅ ከሰብለ እስከ እስክንድር ከእስክንድር እስከ ለጥቅም አዳሪ ተቀጣሪ ሰላዩች ባለ ንፁህ ነብሷን ዕፀህይወትን በምሬት ጥላ ትሄድ ዘንድ እያመቻቿት ይገኛሉ ይህ የምሬት ሴራ ይሳካ ይሆን ግዜ ደጉ ድራማው መልሰ አለው እንዲሁም የወረሰችው ሃብት ሰላም የነሳት ዕፀህይወት በድል መንገድ ይህን ውስብስብ የተንኮል ድር በጥሳ ትወጣ ይሆን ዕፀህይወት ድራማ አሁንም መልስ አለው ።
የአባቷ ውርስ ከሌላ በሚወለድ ሰጋ ወንድም ፣ የህግ እናት አይገባትም በሚል በወንድሟ አጉል ፍላጎት ፈተና ውስጥ የገባችው ዕፀህይወት ፣ የእስክንድር እና እናቱ ሰብለ የውስጥ ክፋት የልጁ ስልጣን መጠማት በታሪክ መስዋዕትነት የተከፈለበትን ድርጅትን ባል በሰል አእምሮ በመፈለግ ብቻ ለመምራት የሚመኘው እስክንድር በክፋት ሆኖ የዕፀህይወት እናት ቤት የሚባለውን የገጠር ቤት በእሳት አንደደው።
በጋራ በመምከር ከነሰብለ ጋር ሆነው ሳለም ምንም እንዳልተፈጠረ ሆነው ከከተማ እርዳታ በመያዝ ለጥየቃ መሄዳቸው ምን ያህል ለሃብት ፣ ለስልጣን ነብስ የሸጡ መሆናቸውን የሚያሳይ ነው።
ለብቻው ከጀርባዋ የሚከወን ሁሉ የክፋት ግብርን ከደግ ነብሷ ጋር በስውር የሚመክተው የዕፀህይወት ልብ በዚህ መንገድ በየዋህነት መዝለቅ ይችላል መገመት ይቻላል።
ዕፀህይወት በአባቷ የተሰጣት ሃብት የመከራ ምንጭ የደስታ መጋዝ ሆኖባታል ፣ ወንድሟ የህግ እናቷ በሀገሬ ቢህል በእንጀራ አናቷ በአባቷ ሚስት ጥርሰ የተነከሰባት ልጅ ሃብት ሲከተላት ፣ የቅርብ የምትለው ቤተሰብ ኑሮን የመከራ ዝናብ ለማድረግ እየጣሩባት ነው በጀርባ በማሴር የሚበቃውን ሃብት ለማጥፋት በጥረት ላይ ናቸው ።
በርግጥ የሰው ልጅ የሚዘነጋ የህይወት ዋጋውን በተመለከተ አስተዋሽ የሚፈልግ ነው ሁሌም የስጋ ፍላጎቱ የሚያሸንፈው ፣ ነብሱን የሚረሳ ነው የእነ ሰብለ ፣ እስክንድር መልክም በዚህ አግባብ የሚታይ ነው በህይወት መንገድ ደሞ ልክ እንደ ዕፀህይወት ነብስን በማስቀደም መኖር ዋጋ እንዳለው የሚያምኑ በዙሪያችን ብዙ አሉ ያጡ የሚመስሉ ግን ብዙ ያላቸው ሆነው የዘገዩ የሚመስሉን የፈጠኑ አሉ ዕፀህይወት ከዚህ የምትመደብ ናት ሴራ ክፋት ተደግሶላት ያለ መከላከያ የልብ ተግባሯ የሚመክትላት በጎ ነገር ሁሌም ጥላ ከለላ የሚሆናት ብርቱ ተግባር ያላት ሆና ያለች ናት ።
የእስክንድር እናት ሰብለ የልጇን ጥፋት ለመሸፋፈን በጥረት ላይ ናት እውነት በልሳን ታወራ ይሆናል የሰሩት ስራ የበደለ ጥግ በተለይ የእስክንድር ስሜታዊ መሆን ቶሎ መናደድ የጥበብ መጉደል የሽንፈት ምንጭ እየሆነ ነው ፍላጎት ብቻ ዋጋ እንደሌለው ማወቅ አልቻለም ስክነት የጎደለው መንገድ መጨረሻው ውድቀት ነው የዚህ ቤተሰብ የሴራ ካባ የሚገለጠው በዚህ ልጅ የመሆኑ ነገር ግልፅ ይመስላል።
ሰብለ ወዳጅ መስሎ ጠላት መሆን ላይ የተካነችበት ነው በተለይ ማስመሰል የብቻዋ ነው በዚህ መንገድ ነው የዕፀህይወት አባትን ከገጠር ሚስቱ ጠቅልላ በመያዝ የግለ ያደረገችው ነገሩ የዕፀህይወት አባት የዕፀህይወት እናትን ያገባት ለስልጣን ወይም ለስራ ሃይል ዘመድ ፍለጋ ትዳር ቢይዝም የሰብለ ሚና የከተማ ሚስት ሆና ጉልበት ትይዝ ዘንደ ያላት የማስመሰል ብቃት የሚናቅ አይደለም ፣ በሴራም ቢሆን የዋዛ አይደለችም ።
የልጇ መቸኮል ግን መስመር መሳቱ ሌላው የመከራ ቀን መጀመሪያው ማሳያ ሊሆን ይችላል ፣ ሌባ ሲሰርቅ መስማማቱ ፍቅሩም ቢሆን ወፍ ያረግፋል ፣ ችግሩ ሲካፈል ነው ይሉ እስክንድር እና አሸናፊ የጦፈ ፀብ ውስጥ ይመስላሉ ነገሮች ከረዋል የሁለቱ መጣላት እልፍ የተደበቁ ሚስጥሮች መጋለጣቸው አይቀሬ ነው በቀጣይ ዕፀህይወት ድራማ በማይጠበቅ መቼ መከሰቱ አይቀሬ ነው የሁለቱ ፀብ ይፋ መሆን የሚንደው የሴራ ካብ ብዙዎችን እርቃን የሚያስቀር ነው የዕፀህይወት መጎዳት ፣ የጀርባ ክፋት በማጋለጥ ሰላም ያመጣ ይሆናል ።
ክፋት ያማረራት ለመጥፋት የወሰነችው ዕፀህይወት አማራጭ የሚሆነው መበርታት መሆኑን ተረድታ ለመጋፈጥ ትወስን ይሆን መሸሽ ዋጋ አልቦ መፍትሔው ዘላቂ አለመሆኑ አጢናበት የቸገረው ድመት ነብር ይሆናል ይሉ በንስር ጉልበት ተነስታ ነገሮች ተገልብጠው ታሪክ ታስቀጥል ይሆን ወይስ ጥፋት የዋህነትን መደበቂያ በማድረግ ተሸንፋ እውነትን ጥላ ሃቅን በማኮሰስ ትቀር ይሆን ድራማው መልሰ አለው ።
ለወትሮ የአንበሳ እና የሚዳቆ ውድድር ላይ ሁሌም አሸናፊው ሚዳቅ ነው አንበሳው ለሆዱ ሚዳቆ ለነብሷ ነውና ትግሉ ሁሌም አላማ ይዞ ፣ እውነትን አስቀድሞ የሚጓዙ አሸናፊ ናቸው ዕፀህይወትም በዚህ መንገድ ናት ማሸነፏ አይቀሬ ነው ትምህርት ከዘለቀው ህይወት የሞረደው ብርቱ በመሆን በሌላ ገፅ መከሰቷ አይቀሬ ነው ።
በዚህ ድራማ ላይ የትግሉ ውጤት ቀያሪ አላማ በመሆኑ የሰራዊት ብዛት ጦርን ድል አያደርግም ምክንያት እንጂ ፣ ህይወትም ቢሆን በዚህ ልክ የተሰራ በተፈጥሮ ህግ የሚመራ እውነት የሚገዛው ፍርዱም ቢሆን ልክ ቢዘገይም እንኳ በልኩ የሚክስ ጉርሻ መደለያ ፈፅሞ አይገዛም ዕፀህይወትም ይህ የተፈጥሮ ህግ ይረዳት ይሆናል ።
ወርቃማውን ነገ በአላማ አስቦ ፣ ፍቅርን በማስቀደም ህይወትን አሸንፍ ድል ከእኛ ጋር ሆና እልፍ እስኪከተልህ በእውነት መፅናት ለዕፅህይወት መፍትሔ የድል ካርድ ነው ።
ህይወት በዕፀህይወት መልኳ ብዙ ነው ፣ የሰው ልጅ የማይገመት ረቂቅ ፍጡር ነው ፣ የስጋ ፍላጎት ነብስን ያስታል ፣ ፍቅር ዋጋ አቶ ስሜት ፍላጎት ትልቁን ሰው ሸወዱት ፣ መታመን ለራስ መሆኑ ተዘነጋ ፣ ደግ ማድረግ የሰማይ ስንቅ መሆኑ ተረሳ ፣ ማስመሰል ለሆድ ፍላጎት እንጂ ለታሪክ መሆን እንደ ማይችል ማወቅ ጠፋችው ፣
መልካም ነብስ ግን ጠባቂ ያላት መሆኗን ማወቅ አቃታቸው የስጋ አዳሪዎች ፣ ፍቅር ነጠፋ ፣ ደግም ኮበለለ ።
ዐፀህይወት ባለ ብዙ መልክ ነው ጎራ ይበሉ የሚባክን ግዜ የለም የህይወት አስተማሪ የሰርክ መልከ ነው ።