ድራማው በሰኔ ወር ልባችን አንጠልጥሎ ትቶናል፣ ግን ገና ጅማሬው መሆኑን አላወቅንም ነበር። በወሩ መጨረሻ የአቦል ገጸ ባህሪያት ምን ላይ ትተውን እንደነበር እናስታውስ፡
ግዛት [ከሰኞ - ረቡዕ ከምሽቱ 2:30]
የሀረግ ፍጹም ቤተሰብ በውሸት እና ክህደት የተሞላ በመሆኑ ንግስቷ ሀረግ በድርጊቷ እየተጸጸተች እንደሆነ ተረድተናል። ነገር ግን ጸጸት አሮንን መልሶ ወደእሷ ማምጣት ስለመቻሉ እርግጠኛ አይደለም… የእናት ፍቅር የሚመልሰው ከሆነ በጉጉት እየተጠባበቅን ነው።
ዕፀህይወት [ሀሙስ እና አርብ ከምሽቱ 2:30]
ዕፀህይወት በአባቷ ያልተጠበቀ ሞት ሀዘኗን ሳትጀምር አባቷ ያላወቀችው ትልቅ ነገር መኖሩ ይጋለጣል። አባቷ የማታውቀው ሁለተኛ ቤተሰብ ነበረው እና ቤተሰቡ የአባቷ ግዛት ለመረከብ የዕፀህይወት እና እናቷን ህይወት አደጋ ውስጥ ከመጣል ወደኋላ አይሉም። የዕፀህይወት አለም በጥቂት ቀናቶች ውስጥ ተደበላልቋል እና ይሄን ጥያቄ አሳድሮብናል፡ ዕፀህይወት ማንነቷን ሳታጣ ይሄን ፈተና ታልፋለች ወይስ ተሸንፋ የማትፈልገው አይነት ሰው ትሆናለች?
ፍርቱና [ሰኞ ከምሽቱ 2፡00]
ድራማው የጀመረው በሮማን ግድያ ላይ ባለቤቷ ካሌብ እጁ ለበት የሚለውን ልብ አንጠልጣይ ጥያቄ በማንሳት ነበር። ነገር ግን ይበልጥ የካሌብ እና ሮማንን ታሪክ ስንረዳ ሁሉም ነገር እንዳሰብነው አለመሆኑን ተረድተናል። ነገር ግን አሁንም ጥያቄ እንድ አይነት ነው፡ ሚቱን ገድሏታል? እና ምስጢራዊዋ ገጸ ባህሪ ማክዳ ከግድያው ጋር ምን ያገናኛታል?
አዲሱ መዝናኛ በአቦል፡ ፓይለቶቹ ሐምሌ 15 ይጀምራል
ፓይለቶቹ የቤተሰብ ይዘት ያለው ድራማ ሲሆን የሁለት አብሮአደግ ጓደኛሞች የህይወት ውጣ ውረድ የሚያሳይ ድራማ ነው። በዋና ገጸ-ባህሪያት መኮንን እና አሌክስ የስራ ዘርፍ አማካኝነት በፓይለቶች የስራ ቀን ምን እንደሚመስል ማወቅ እንችላለን። መኮንን እና አሌክስ በህልማቸው ምክንያት ጓደኝነታቸው ይፈተናል። ጓደኝነታቸው ያሸንፋል ወይስ ይሄ ፈተና ይለያያቸዋል? ፓይለቶቹ ማክሰኞ ሐምሌ ከምሽቱ 2፡00 በአቦል ቲቪ ይጀምራል!
የሚወዷቸውን መዝናኛዎች በአቦል ቲቪ፣ ዲኤስቲቪ ቻናል 465 ይከታተሏቸው!