አቦል ቴሌቭዥን ለመዝናናት ፣ ለቁምነገር ፣ ታሪክን ተከትሎ ህይወት ለሚቃኝ ድራማ ፣ በሚፈስ የመቼት ውጤት በተሟላ የታሪክ ፍሰት ተመራጭ አይን ማረፊያ የሆኑ ተከታታይ ድራማዎችን ማቅረብ ላይ የሚገኘው ባለ ብዙ አማራጩ ነው ።
አቦል ቴሌቪዥን በአዲሱ አመት በተወዳጅ ተከታታይ ድራማዎች ላይ ያሉ አይረሴ ገፀባሕርያት በምን መልኩ ይከሰቱ ይሆን ከሰመረ እስከ ሃረግ ከሃረግ እስከ አሸናፊ ልበ እርግብ ዕፀህይወት እንዲሁም የንዋይ ፍቅር ያከነፋት ሰብለ በአዲሱ አመት በምን ይከሰቱ ይሆን ።
የሁሉም ልብ ምት ነው ባህሪ የሚቃኝ የሁኔታ ውጤት የሃሳብ መውጣት የኑሮ ደረጃ የሚቀርፀው ነው እና በአዲሱ አመት በልዩ መልክ ዘመን ሲተካ አብሮ ውጥን ይኖራል እና የተወዳጁ አቦል ቲቪ ተከታታይ ድራማዎች ገፀባህርይ በዚህ አመት ከግዛት ድራማ ሃረግ በእኩይ የተሞላች ድርጊት ኩነኔ ወደ ትክክለኛው የሰውነት ልክ ባህሪ ትመጣ ይሆን ማን ያቃል ግዜ በውስጡ ሚስጥር ተሸክሟል ፈራጅ አልቦ መሆን የግድ ሆኖ እንጂ ሃረግ ከተንኮል ይልቅ ከቅንነት ፣ ከፀብ ይልቅ ፍቅርን በማስቀደም ወደ ባህሪዋ ትመለስ ይሆን ወደ ሚገባት ምኞት ግዜ ደጉም መልስ አለው ከድራማው ባሻገር
በግዛት ድራማ ሃረግ መልካም ምኞት እሷም ይኖራት ይሆን ሰውነት ዝቅ አይል በድርጊት ቢሸፈን በፍርድ በህሊና ባለቤት በመሆኑ በፀፀት ሆና ትመኝ ይሆናል በአዲሱ አመት ።
ሌላው የአቦል የታሪክ ድምቀት ትዳር ይዞ አይኑን በአይኑ ያየው ምሳሌ መግደል የክፋት ጥግ የጭካኔ መሪ የክፋት ውሃ ልክ ሰመረ ክፉ ገዳይ በአዲሱ አመት ልጅ በመውለዱ ልቡ ራርቶ ወደ ደግ መከወን ይመለስ ይሆን የአዲስ አመት ምኞት ነው ፣ ሰመረ ያለ ምክንያት ነብስ ያጠፋል ፍቅር ፣ ማዘን ፣ እኔ ብሆን ፣ የሚሉ ነገሮችን አያቅም ፈፅሞ ብቻ ከዚህ ሁላ ነገር ወቶ ልጁ ልብ ሰታው ይመለስ ይሆን ወደ ትክክለኛ ህይወቱ በአዲሱ አመት አሁንም ምኞት ነው ።
እንዲሁም የዕፀህይወት ድራማ ማልያ ብዙ አሸናፊ በተለዋዋጭ ባህሪው ይዘልቃል ወይስ መንገዱን መርምሮ አዋጭ አይደለም በሚል ወደ ራሱ ይመለሳል በአዲሱ አመት ግዜ መልስ አለው አሸናፊ በማስመሰል የተዋጣለት ነው ሁሉንም ሃሳብ በማስመሰል ነው የሚያልፈው ከፅህይወት ጋር ያለው ግንኙነት ጭምር በእስስት ባህሪው ወዳጅ መስሎ መቅረቡ ዕፀህይወትን ዋጋ በማስከፈል እረገድ ሚናው ትልቅ ነው ይህን ባህሪውን ይዞ ወደ አዲሱ አመት ይሻገር ይሆን ድራማው መልስ አለው ግን ግን በዚህ መልኩ መቀጠሉ ለህልውናው አስጊ በመሆኑ ውስጡን አድምጦ ለስጋዊ ፍላጎት ሳይሆን ለነብስ ሲል የሚኖር ያድርገው በአዲሱ አመት ምኞትም ፣ ምርቃትም ነው ብቻ ይመልሰው ።
ምክንያቱም ለጥቅሙ ሲል የማያደርገው የለም ፍላጎት ከነብስ የሚበልጥበት የባህሪ ልዩነት ግድ የማይለው አስመሳይ ሰው ዋጋ የለውም እና ቢቀርበት መልካም ነው ።
የአባቷ ውርስ ከሌላ በሚወለድ ሰጋ ወንድም ፣ የህግ እናት አይገባትም በሚል በወንድሟ አጉል ፍላጎት ፈተና ውስጥ የገባችው ዕፀህይወት ፣ የእስክንድር እና እናቱ ሰብለ የውስጥ ክፋት የልጁ ስልጣን መጠማት በታሪክ መስዋዕትነት የተከፈለበትን ድርጅትን በችኮላ ልምድ በሌለው አእምሮ በመፈለግ ብቻ ለመምራት የሚመኘው እስክንድርን በመርታት የተሰጣትን አደራ የቤተሰብ ታሪክ የአባቷን የንግድ ጀብዱ በንስር ጉልበት በመነሳት ወደ ፊት መታ መምራት ትችል ይሆን በአዲሱ አመት ዕፀህይወት መልካም ምኞት ነው ወይም ከጀርባዋ የሚከወኑ የሃብት ማሳጣት ስራዎችን በማምከን ወደፊት ትመጣ ይሆን ልበ እርግብ ዕፀህይወት ድራማው መልስ አለው ።
ዕፀህይወት የአባቷን ውርስ በተመለከተ ብዙ መጓዝ አለበት ነገሮችን በመረዳት የውስጥ ፍላጎትና በመተው ታሪክ ማስቀጠል ላዮ ትኩረት በማድረግ በአዲሱ አመት በባህሪ ለውጥ ትከሰት ይሆን ግዜ መልሰ አለው ።
እንዲሁም ሰብለ ተንኮል ትታ ወደ ራሷ በአዲሱ አመት ትመለስ ይሆን በቅንነት ይበቃል በማለት ግዜ መልስ አለው ሰብለ የምድርን የሰው ልጅ ፈተና በማራኪ የታሪክ ፍሰት በልኩ የሚተርከው ዕፀህይወት ድራማ በመቼት ፣ ግጥምጥሞሽ ታጅቦ ወደ አዲስ ውስብስብ የትዕይንተ ምዕራፍ በመሸጋገር ሂደት ላይ የራሷን የታሪክ ሚና ስትወጣ የነበረች ናት ዛሬ በዚህ መልኩ በአዲሱ አመት ትቀጥል ይሆን አዲሱ አመት መልስ አለው ።
የዕፀህይወት ደጋፊዎች የሃሳብ የሞራል ፣ አማካሪ መመኪያዎች በሞት ሲለዩ ለብቻዋ መቅረቷ በተቃራኒ የቆሙ የሃብት ተፋላሚዎች በአገኘውሽ ስሜት በደስታ ሆነው የተንኮል ሴራ በመሸረብ ላይ የነበሩት ወደ ቀልባቸው ይመለሱ ይሆን ግዜ አዲስ አመት ይመልሰው ።
መቼም አዲስ አመት ሁሉም የሚታቀድበት እንቆቅልሽ መልስ የሚያገኝበት ነው በሃይል የሚጀመር ህይወት ያለበት ሰው ሁሉ ወደፊት የሚራመድበት ነው በዚህም አመትም የፍርቱና ድራማ በወንጀል የተሞላው ወንጀሉ ተጋልጦ ድብብቆሽ ይቅር ይሆን እንዲሁም ስምን መልአክ ያወጣዋል ይሉ የግርድ ድራማ ሚስጥር የሚገለጥበት ዘመን ይሆን በዚህ ድራማ ሁሉ ነገር ሚስጥር ነው አዲሱ አመት ግን ይህን በአዲሱ ይተካ ይሆን ድራማው መልሰ አለው ።
አቦል ቴሌቪዥን በአማራጭ የተሞላ ፣ በአዲስ ክስተት የሚታወቅ የመዝናኛ አማራጭ ማዕድ ነው በዚህ አመትም ተወዳጅ ድራማዎችን ይዞ በአብሮነት ይዘለቃል መልካም አዲስ አመት ።