Logo
Dinknesh S1

ድንቅነሽ ባለ ብዙ መልክ ።

ዜና
23 ፌብሩወሪ 2025
የህይወት ገፅ የፅናት እና የዳግም ብስራት መንገድ በአጀብ እንዲሁም በእክል የተከበበ ጉዞን የሚያስቃኝ አጭር ድራማ ።
Dinknesh

የምድር ገፆች የኑሮ መልኮች ብዙ ናቸው ዘርፋቸው በመልክ እና በባሃሪ መጠን የሚጠቀሱ ሲሆኑ የፍላጎት የመድረስ ልካችን የሚመዝነው  በጥረት በብርታት ነው በድንቅነሽ አጭር ድራማ መውደቅ መነሳት ሃሜት ፍቅር ፅናት የህይወት አላማ በእኩል ለአንዲት ውብአለም ለተባለች እንስት አይበገሬነት ባህሪ የሰርክ መገለጫ ለሆናት ልጅ በአማራጭ ሳይሆን በግድ መታለፍ በሚገባው ውድድር ውስጥ ደረጃ በደረጃ የሚከሰቱ ናቸው እሷም በትሆን የማትቀመስ የእሳት ምሳሌ ናት

እንዲሁም በአንድ ጀንበር ሳይሆን በሂደት በልፋት የመጣ የስራ ስኬት ያላት ታዋቂ የጥበብ ሰው ተዋናይ ናት ጋን ተሸካሚው ይሉ በፅዳት ተቀጥራ የምትሰራበት ትያትር ቤት ሰርክ በምታፀዳው መድረክ ላይ የነገሰች በሀገሪቱ በሞያ ስኬት በድባብ ያለች ናት ችግር ብርቄ አይደለም በሚል ሁሉንም እክል በጀግንነት የሳሙና ረይሳ በማድረግ ከደመናው ከችግሩ በላይ ስትጓዝ የሚያሳየው ይህ ድራማ ብዙ የገሃዱ አለም መልኮችን አንግቦ ልብ አንጠልጥሎ በተደባለቀ ስሜት የሚያስጉዝ ስምን ከግብሩ ጋር ያጣመረ ድንቅ ድራማ ነው

የድንቅነሽ አፅመ ታሪክ የድራማው መሪ ባለ ታሪክ ውብአለም የተባለችው ጠንካራ እንስት ከህይወት የመጨረሻው ደረጃ ማጣት መንጣት ተነስታ ከፍተኛ የሚባል የእውቅና ደረጃ ላይ የደረሰች ናት ይች እንስት በልጅነት ዘመኗ ደመ ግቡ ባለመሆኗ  የመልከ ጥፉ መግለጫ የሆኑ አንድም ቃላት ሳይቀሩ የተባለች በድህነት ያደገች መገለል መሰደብ ማጣት መከልከል ብርቅ ያልሆነባት አለት ናት እነሆ በውጣ ውረድ ድህነትን አሸንፋ ገንዘብ ዝና ሲመጣላት የሀገሬ ጋዜጠኞች የኋላ ታሪኳን የድህነት ዘመኗን በመተረክ በሃሜት በስም ማጥፋት ዘመቻ ወደኋላ ለመመለስ ልፋቷን ውሃ ሊቸልሱበት በደፋ ቀና ላይ ናቸው እሷም በትግል በፅናት ቆማ ስትታገል በሌላ መልኩ የሚያሳየው ድንቅነሽ አጭር ድራማ ኩራት ስም ዝና ቅናት ገንዘብ በህይወት ትግል ውስጥ ስጋ ለብሰው ለድል ሲተጉ ያሳያል

በድንቅነሽ አጭር ድራማ ውስጥ የውስብስብ ህይወት አካል የሆኑ ጥቂት የማይባሉ ባለ ታሪኮች አሉ እነሆ እነማን በምን ገፀባሕርያት ምን ወክለው ለሚለው ጥያቄ ወደ ተወዳጅ አቦል ቴለቪዥን ጎራ ይበሉ

ድንቅነሽ አጭር ድራማ ትጋት ስም መጥፋት ክፋት ገንዘብ ስኬት ትከሻ ለትከሻ ይለካካሉ

#ድንቅነሽ ዘወትር አርብ ከምሽቱ 2፡00 በ #አቦልቲቪ ዲኤስቲቪ ቻናል 465 እንዳያመልጥዎ!

 #MyDStv አፕ አሁን አገልግሎቱን ያስቀጥሉhttps://tinyurl.com/yc8p3xvd እና  DStv Stream App የሚወዱትን የአቦል ቲቪ ድራማዎች ይመልከቱ፡ http://tinyurl.com/bdh2j9ed