Logo

በሰራተኛ ፈልጉልን ከሱዚ እና ዜና ጋር ያሳለፍናቸው 3 ምርጥ ጊዜያቶች

ዜና
21 ኤፕሪል 2025
የሰራተኛ ፈልጉልን ምዕራፍ 2 ፍጻሜ ደርሷል።
Serategna feligulin S2 article cover

የሰራተኛ ፈልጉልን ምዕራፍ 2 ፍጻሜ ደርሷል። ተወዳጁን ሲትኮም ድራማ ከመሰናበታችን በፊት ግን በጣም ያዝናኑንን የሱዚ እና ዜና አስቂኝ ጊዜያቶ እንመልከት።

  1. ሱዚ ጣም ያለውን ምግብ ከቤት ያገደች ጊዜ!

የመጀመሪያዎቹ የሱዚ እርግዝና ወራቶች ምግቡ ሁሉ ያቅለሸልሻት እና ያስመልሳት ነበረ። ነገር ግን ሱዚ ይሄንን ችግር ብቻዋን መጋፈጥ ስላልፈለገች ቤት ውስጥ የሚሰራው ምግብ በሙሉ እሷን የሚስማማ ካልሆነ ምንም እንዳይሰራ ታዛለች።

  1. ዜና በሱዚ ዶክተር ይቀናል...

የሱዚ እርግዝና በመጀመሪያ ወራቶች ላይ ብዙ አሳሳቢ ገጠመኞች ነበሩ ስለዚህ ሱዚ የተለያዩ ዶክተሮችን አግኝታ ነበር። ከእነዚህ አንዱ ዶክተር ማሳጅ የሚያደርግ ነበር እናም ዜና ሱዚ ምን ያህል እንደተደሰተችበት ሲሰማ ቅናት ይይዘዋል!

  1. ሱዚ ዜና ከሌላ ሴት ጋር እየማገጠ ነው ብላ ታስባለች

በአስቂኝ አለመግባባቶች ምክንያት ሱዚ እርግዝናዋ መልኳን ስለቀየረው ዜና ከሌላ ሴት ጋር እየማገጠ ነው ብላ ታምናለች። የጠረጠረችው ሰው ማንነት ግን ያልታሰበ ሰው ይሆናል።

ከሱዚ እና ዜና ጋር በነበረን አስቂኝ ጊዜያት በጣም ያዝናኑን እነዚህ ነበሩ! እርስዎ የወደዷቸው ጊዜያቶች ምን ነበሩ? በማህበራዊ ሚዲያ ገጻችን ያሳውቁን።

በ #MyDStv አፕ አሁን አገልግሎቱን ያስቀጥሉ: https://tinyurl.com/yc8p3xvd እና በ DStv Stream App የሚወዱትን የአቦል ቲቪ ድራማዎች ይመልከቱ፡ http://tinyurl.com/bdh2j9ed