Logo

ሚስቶች ለሁለት ተከታታይ ጊዜ ድል ቀንቷቸዋል።

ዜና
28 ፌብሩወሪ 2025
በሁለት ጓዳ በተከታታይ ሳምንት የእናቶች መሸነፍ ሚስቶችን ደስ አላሰኘም ፥ እናቶች አሸናፊ ቢሆኑ ደስተኛ መሆናቸውን የገለፁት ሚስቶች ግን አልሆነም ፥ ውድድር ሆኖአል እና ባልም የማን ይሁን የማን ማወቅ አይችልም መቼም መሸነፍን ሚስቶች ቢፈልጉም አልሆነም ።
Hulet Guada S1

 

ባል በሚስት እና በእናቱ ማህል ያለውን የሞያ ልዩነት መለየት አልተቸገረም ወይም የምግብ ጣዕም  በመቅመስ አይደለም በማሽተት እንኳን መለየት ይችላል ይባል የለ በቀላሉ ለይቶ ሚስቶች አሸናፊ ሆነዋል በዚህ መሰናዶ እጅጉን ደስ የሚል የሚስት እና የእናት የምግብ ዝግጅት ውድድር በጊዜ የለኝም መንፈስ የጦፈ ውድድር ሆኗል የማብሰያ ቦታ ሰፊ ሁሉም የሞላበት ማዕድ ቤት በፍቅር የማብሰል የሞያ መለየት ውድድር የትስስር የሚስት እና እናት ፍቅር የሚጠነክርበት የጋራ መተሳሰብ የሚታይበት ግሩም ትዕይንት በመሆን ላይ ይገኛል ሁለት ጓዳ ። 

እነሆ ሁለት ጓዳ ድብልቅልቅ ስሜት የሚታይበት ሆኗል እናቶች በሚስቶች መረታታቸው  ለሚስት ምቾት የሚነሳ ሆኗል እንዲሁም የእናቶች በሚስቶች መከበር የባሎች እረፍት ነው ለሚስቶች ደሞ የነገ እናት በመሆናቸው የህይወት ዋስትና የመኖር ጉጉትን የሚያንር ነው እናቶች ከክብር በላይ ይገባቸዋል የተፈጥሮ ውህደት በሚገባው መልኩ መገለፁ ጭምር የደስታ ማዕዘን የፍቅር ጥግ የሚታይበት መድረክ ጭምር ሆኗል ሁለት ጓዳ በእናት እና በሚስቶች መካከል የሚደረገው የሞያ መለየት የውድድር መድረክ ። 

እናት  ቅኔ ናት፤ ከተባለላት፣ ከተጻፈላት፣ ከተዜመላት በላይ የረቀቀች ረቂቅ ቅኔ ናት። 

እስከዛሬ ከያኒያን ስለሴት ከተራቀቁት፣ ከተጠበቡት ሁሉ እኔ ለማውቃት ሴት ሁሉ የሚመጥኑ ሆነው አይታይም በዚህ መሰናዶ ሚስቶች ለእናት የሰጡት ክብር እራስን ከማሸነፍ የሚመጣ ነው ። 

የሴትነት ጸጋው ብዙ ነውና የሴትን ትክክለኛ ማንነት መርምረን አጥንተን የደረስንበት ውስጠ-ስሪቷን አጥንተን የገባን ይመስላል ወይ ብሎ መጠየቅ ዋጋ አለው ። 

እናት አስተማሪ ናት ከታላቅነቷ፣ ከብልሃቷ፣ ከረቂቅነቷ፣ ከመግዛት አቅሟ፣ ከርህራሄዋ፣ ከሰላማዊነቷ ከሌሎችም አያሌ በረከቶች አንጻር ለእናት  የተደረገላት፣ የተነገረላትና የሆነላት ሁሉ ያንሳል ። 

በሁለት ጓዳም ቢሆን የእናት ክብር ከፍ ብሎ ይገኛል ሚስቶች የሰጡት ክብር በዚህ መልኩ የተቃኘ ነው በሁለት ጓዳ መልከ ብዙ ፈተናዎች ፣ የደስታ ጥግ ፣ የእዝነት መልክ የፍቅር ገፅ የመተሳሰብ ነገር በሁለት ጓዳ ነብስ ዘርተው ይታያሉ በሁለት ጓዳ ። 

አናት የፍቅር ጥግ ናት የመውደድ ምሳሌ የዘመን መገለጥ የተፈጥሮ ውህደት የማትሰለች ውድ ናት እና  የእናት ክብር ሁሌም መኖር የሚገባው ቢቻል እማ ብዙ በተሰጣት እንኳን ክብር ነብስ ይገባታል በትክክል ማሰብ ከቻል ሁለት ጓዳ በተከታታይ ሳምንት ይህን ስሜት በከፍተኛ ደረጃ በተወዳዳሪነት የመጡ ሚስቶች አሳይተዋል በሁለት ጓዳ መተሳሰብ አግር አለው ፍቅር፣ ክብር ፣ ለእናት ሆኖ መስዋዕትነት ዋጋ ተሰጥቶት ታይቷል በሁለት ጓዳ ።

#2ጓዳ ዘወትር ረቡዕ ከምሽቱ 3፡00 በ #አቦልቲቪ ፣ ዲኤስቲቪ ቻናል 465 ይጀምራል!

በ #MyDStv አፕ አሁን አገልግሎቱን ያስቀጥሉ: https://tinyurl.com/yc8p3xvd እና በ DStv Stream App የሚወዱትን የአቦል ቲቪ ድራማዎች ይመልከቱ፡ http://tinyurl.com/bdh2j9ed