ስፍራሽብዙ ልምድ እና እውቀት ከሀገር ፍቅር ጋር ያዛመዱ በመሆናቸው በተማሪዎቹ ላይ የሚታይ የባህሪ ለውጥ መታየት ጀምሮአል በጎሪጥ የሚተያዩት ተማሪዎች የሰርክ ጠብታ አለት ይንዳል ይሉ በጊዜ ሂደት መቀራረብ ፣ ያለፈ ህይወት ፣ የልጅነት አስተዳደግ የቤተሰብ አጠቃላይ ምንነትን ማውራት ጀምረዋል በዚህ ሂደት ውስጥ የተገነቡበት የልጅነት ውቅርን መመርመር ይዘዋል ።
መታረም ይገባቸዋል የባህሪ ለውጥ አስፈላጊ ነው በዚህ አመል መዝለቅ አትችሉም በዚህ ባህሪ ከራስ አልፎ ለሀገር የምትሰሩ መመኪያ መሆን አትችሉም የተባሉበት ባህሪ መሰረቱ የቤተሰብ አስተዳደግ የልጅነት ውጤት መሆኑ በመነጋገር ተቀራርቦ በማውራት ማወቅ ተችሎአል መቼም የልጅነት አስተዳደግ የቤተሰብ ሚና በልጆች ህይወት ሁለተናዊ ምንነት ላይ ተፅእኖው የማይገመት ነው ፣ ቤተሰብ የተገራ ሙሉ ስብእና ካለው ልጆች በዛው ልክ ተመራጭ ቤተሰብ አመስጋኝ የሚኮራባቸው ይሆናሉ ልጅ የሚበላሸው በተቃራኒው ቤተሰብ ሲሆን ነው ጦስ መሸማቀቅና በልጅ ማዘን የሚመጣው ።
የተማሪዎቹ ከመስመር መውጣት መሰረታቸው የልጅነት አስተዳደግ ቤተሰብ መሆኑ አሁን ላይ የተደረሰበት ሲሆን ስፍራሽብዙ ከዚህ በኋላ ምን ልታደርግ ይሆን የሚለው ነገር አብይ ጉዳይ ነው እሳቸው በአሰተዳደግ የሚታሙ አይደሉም በጌም ዘመናዊ ጨዋታ የመጡ ፣ በኮሪያ ፊልም በሆሊውድ አክሽን ፣ በህንድ የፍቅር ፊልም አላዩም በልጅነት ምንነት መሰረታቸው ይልቅስ
በቱባው በሀገርኛ በተገራው የልጅ አስተዳደግ ውስጥ ያለፉ ናቸው ስለዚህ የልጅነት ወለምታን ጥንስሱን እንዴት ያክሙት ይሆን ድራማው መልስ አለው ።
በርግጥ የተማሪዎቹ ባህሪ የልጅነት የቤተሰብ አጉል ልጆችን አንቀባሮ የማሳደጉ ነገር በአስተውሎት ለተመለከተው ግልፅ ይመስላል ምክንያቱም የሳባ ከልክ ያለፈው በራስ መተማመን ከቤተሰብ አጉል ድጋፍ እና ያልታረሙ ድርጊቶች የሚመነጩ ናቸው የሌሎችም ያልተገባው ባህሪ በዚህ መልኩ ነው የመጣው ባይባልም በትክክለኛው መንገድ ክፉ ደጉን አለማየታቸው የቀናው መመልከት ባለመቻላቸው በዚህ ደረጃ ስጋት ሆነዋል ይህ ባህሪ ስፍራሽብዙ የቱ ዘዴ ትመርጥ ይሆን አሁንም ድራማው መልስ አለው ስፍራሽብዙ በተወዳጁ አቦል ቴሌቪዥን ።
#ስፍራሽ ብዙ ዘወትር ሐሙስ ምሽት 2:00 በ #አቦልቲቪ፣ ዲኤስቲቪ ቻናል 465 ይቀርባል!
በ #MyDStv አፕ አሁን አገልግሎቱን ያስቀጥሉ: https://tinyurl.com/yc8p3xvd እና በ DStv Stream App የሚወዱትን የአቦል ቲቪ ድራማዎች ይመልከቱ፡ http://tinyurl.com/bdh2j9ed