Logo

ከእነዚህ የሰራተኛ ፈልጉልን ሰራተኛዎች እርስዎ ማንን ይመርጣሉ? ጥያቄዎችን በመመለስ ያሳውቁን!

ዜና
28 ፌብሩወሪ 2025
የሱዚ እና ዜና ቤት በጣም አስገራሚ ሰራተኛዎች መጥተዋል። እርስዎ ማንን ይመርጣሉ?
serategna feligulin S2 article

ሰራተኛ ፈልጉልን ተወዳጁ የአቦል ቲቪ ኮሜዲ ድራማ በምዕራፍ 2 እያዝናናን ቆይቷል! ሱዚ እንደምትመኘው ልጅ ልትወልድ ነው። ነገር ግን ሱዚ እና ዜና የምትስማማቸው ሰራተኛ እስካሁን አላገኙም፣ በዚህ ምክንያት ጥንዶቹ መስማማት አቅቷቸዋል።

እስካሁን የጥንዶቹ ቤት የተቀጠሩት ሰራተኞች እነዚህ ናቸው፣

ገንዘብ የእራሷን እቅድ ይዛ ነበር የእነ ሲዚ ቤት የገባችው። በመጀመሪያ አብራት የምትሰራዋን ሰራተኛ አባራ ክፍያዋን ማስጨመር ነበር። ነገር ግን ይህ ባለመሳካቱ፣ ፍቅረኛዋን በዘበኝነት አስቀጥራ ቤቱን ለመዝረፍ ነበር ያቀደችው።

እንደልብ ገንዘብን ለማገዝ ነበር የተቀጠረችው፣ ነገር ግን ስራ ከጀመረችበት ከመጀመሪያ ቀን ጀምሮ ከንገዘብ ጋር ተጠማምደው ነበር። ስለዚህ እንደልብ የስራ ጊዜዋን በጠቅላላ ያሳለፈችው ገንዘብን ለማስባረ እቅድ ስታወጣ ነው። በተጨማሪም ገንዘብ ፍቅረኛዋን ካስቀጠረችው በኋላ፣ ከእሱ ጋር የፍቅር ግንኙነት በመጀመር ገንብዘን ታማርራታለች። ነገር ግን በመጨረሻ ሁለቱም ከስራ ተባረዋል።

ጋረድ ሶስተኛዋ የእዚህ ምዕራፍ ሰራተኛ ስትሆን፣ ቤት ውስጥ እንደገባች የጠየቀችው የዋይፋይ የመለያ ቃል ነው። ይህ ዜና እና ሱዚን አያስደስታቸውም ነገር ግን ጣጣዋ እዚህ አያልቅም። ጋረድ የሰው ስልክ የመስረቅ ሱስ አለባት። እናም የሰፈሩን ሰው ስልቅ ስትሰርቅ ቆይታ በመጨረሻ ስትያዝ ተባራለች።

serategna feligulin S2 poll
Serategna feligulin S2 poll 1

እርስዎ እቤትዎ አንዲቀጠሩ አንዳቸውን መምረጥ ካለባችሁ ማንን ይመርጣሉ?

ገንዘብ9%
እንደልብ64%
ጋረድ27%

ሰራተኛ ፈልጉልን ዘወትር ሀሙስ ከምሽቱ 3፡00 በአቦል ቲቪ ፣ ዲኤስቲቪ ቻናል 465 እንዳያመልጥዎ! 

በ #MyDStv አፕ አሁን አገልግሎቱን ያስቀጥሉ: https://tinyurl.com/yc8p3xvd እና በ DStv
Stream App የሚወዱትን የአቦል ቲቪ ድራማዎች ይመልከቱ፡ http://tinyurl.com/bdh2j9ed