በፍቅረኛሞች ወር ላይ ሁላችንም ስለ ፍቅር እና ዘላቂ ግንኙነቶች እንድናስብ ያደርገናል። ግን በዚህ ጊዜ
በህይወታችን ያሉትን ፍቅረኛሞች ብቻ አይደለም የምናስበው፣ በምንወዳቸው ድራማዎች ያሉትን
ጥንዶች መጨረሻ እናስባለን! ስለዚህ እርስዎ የትኞቹን ጥንዶች ፍቅር እንደሚደግፉ በመምረጥ
ያሳውቁን!
የእሳት እራት
በየእሳት እራት ድራማ ላይ የተለያዩ ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪኮች አሉ። በመጀመሪያ ልባችንን የነኩት
ጥንዶች ስሜነህ እና አዲና ነበሩ። ነገር ግን ለበቀል ብሎ የቀረባት ግዛቸው በቀሉን ለማሳካት ብሎ
እንደሚወዳት ዜናን አሳውቋል። ስለዚህ አዲና ማንነቱን ሳታውቅ ወደ ወጥመዱ ከገባች ስሜነህ ለፍቅሯ
መወዳደር አለበት። በሌላ በኩል ደግሞ ምትኬ ስሜነህን ለብዙ ጊዜ በድብቅ አፍቅራዋለች ነገር ግን አሁን
አዲና ተመልሳ ስለመጣች እጅ መስጠት አትፈልግም። ከእነዚህ ጥንዶች እርስዎ የማንን ፍቅር ነው
የሚደግፉት? የማን ፍቅር ይዘልቃል?
ምርጫዎን ያድርጉ
አዲና እና ስሜነህ
አዲና እና ንጉሱ
ምትኬ እና ስሜነህ
አሻራ
አሻራ ድራማ አንድ አንዴ ፍቅር መራራ ነገር እንደሆነ አሳይቶናል። ትዝታ ለአንድ ጊዜ ድክመት ብላ
ከማርቆስ ጋር ትዳሯን አበላሽታለች። ለዚህ ድክመት ደግሞ ዋጋ የከፈለው ባለቤቷ አላዛር ነበር። ከዚህ
ሁሉ በኋላ ግን ማንነቱን ማስታወስ ባለመቻሉ አዲስ ፍቅር ሲመጣ በደስታ ይቀበላል እናም ሌላ ትዳር
ከምስራቅ ጋር መስርቶ ኖሯል። ነገር ግን ወንድሙ አግኝቶት ወደ ከተማ ይዞት ሲመጣ ነገሮች መወሳሰብ
ጀምረዋል። በቅርብ ቀን የቀረቡት ክፍሎች ላይ ትዝታ ባደረገችው ነገር የተጸጸተች ይመስላል። ስለዚህ
የማን ፍቅር ያሸንፋል?
ምርጫዎን ያድርጉ
አላዛር እና ምስራቅ
አላዛር እና ትዝታ
የመረጧቸው ጥንዶች ፍቅራቸው የሚሳካ ከሆነ ላማወቅ አቦል ቲቪን ይመልከቱ!
የእሳት እራት ዘወትር ከሰኞ - አርብ ከምሽቱ 2:30 በአቦል ቲቪ፣ ዲኤስቲቪ ቻናል 465 ይቀርባል!
አሻራ ዘወትር ከሰኞ - ረቡዕ ከምሽቱ 2፡00 በአቦል ቲቪ፣ ዲኤስቲቪ ቻናል 465 ይቀርባል!
በ #MyDStv አፕ አሁን አገልግሎቱን ያስቀጥሉ: https://tinyurl.com/yc8p3xvd እና በ DStv
Stream App የሚወዱትን የአቦል ቲቪ ድራማዎች ይመልከቱ፡ http://tinyurl.com/bdh2j9ed