እነሆ በሁለት ጓዳ የውዷ እናት ፣ የተወዳጇ ሚስት ሞያ ይፈተናል በወንድ ልጅ ለቅምሻ በቀረበው ምግብ አማካኝነት ።
መቼም የወንድ ልጅ የልጅነት ዘመኑ መፈተኛ የእናት ፍቅሩ ነው ። በህይወት ጉዞ የግድ ሆኖበት የተፈጥሮ ውህደት ላይ ትዳር ይመሰርታል ይሄኔ ደሞ የሚወዳት ሚስቱ ሌላዋ የማይደራደርባት የፍቅሩ ስስ የዘመኑ ኩራት ትሆናለች ።
ወንድ ልጅ በትዳር አለም ውስጥ ቢሆንም የእናቱ ፍቅር ከልቡ የማይወጣለት የተዳፈነ እሳት ነው በምንም ሁኔታ ከእናቱ በአካል ቢለይም በመንፈስ በፍቅር ሰንሰለት በእናት ቀና ልቦና ነብሱ በምናብ ከናቱ ናት ይህ ማለት ፍቅሩን ለሚስቱ በጊዜ መስጠት አጋር በመሆን ይገልጻል እንዲሁም ፍቅር መላ እሱነቱን ይሰጣል ።
መቼም ህይወት ፈርጀ ብዙ ናት አታመጣው የላት ይሉ ወንድ ልጅ የሚፈተንበት አንድ ነገር ከች ብሎአል ወይ እናቱን ወይ ሚስቱን የሚያስመርጥ ምንድነው አትሉም ምግብ ነው ምግብ አዎ ምግብ እንዴት ? እሱ ጥሩ በሁለት ጓዳ አማካኝነት አነሆ ሁለት ጓዳ የእናት እና የሚስት ሞያን ወንድ ልጅ በመምረጥ ፍቅር እና ኩራትን ከባዱን ስሜት ይገልጻል በዚህ ዝግጅት ላይ እናት በፊናቸው ልጃቸው የሚያቀውን ያሳደጉበትን የሚወደውን ምግብ ጭምር በሚገባ ስለሚያውቁ ለልጃቸው ከሽነው ምግብ በመስራት ልጃቸው ደሞ የማን እንደሆነም ሳይረዳ ይለያል በማለት በኩራት ያቀርባሉ ።
ሚስትም የባሌን ፍላጎት ያሁኑን ዘመን አመል ከኔ ውጪ የሚያቅ ላሳር ነው በማለት ፈረስ በሚያስጋልበው ማዕድ ቤት (ክችን) ውስጥ በመጨነቅ መጠበብ የኔን ይመረጣል እንኳን ቀምሶ አይደለም አሽትቶ ይለያል በማለት ኮራ ጀነን ብላ በሰፊው መድረክ ይቀርባል ሌላው የባል ፈተናው ጀመረ ማለት ነው ።
ሁለት ጓዳ በዚህ መልኩ አዝናኝ ቆይታ ይዞ በጭንቀት ፣ በኩራት ፣ በፍቅር ፣ በምርጫ አጣብቂኝ ስሜት ውስጥ የሚከት ድንቅ ዝግጅት ነው ።
በዚህ ዝግጅት ውስጥ የእናት ሞያ እና የሚስት ሞያን ባል በሌላው መልኩ የእናቱ ልጅ ፊቱን በመሸፈን የማን ምግብ እንደሆነ ይለያል ይህ ስሜት በቦታው ላለው ሰው ከባድ ነው አስቡት እስኪ ወዲህ እናት ወዲህ ደሞ ሚስት የህይወት አጋር ምግቧን ሳይመረጥ በሞያ ብቃት በባሏ ሳትለይ ስትቀር ምን ይፈጠራል ከባድ ነው። እንዲሁም እናት ሳይመረጡ ሲቀር በምግብ ሞያቸው ያሳደጉት ልጅ የምግብ ሀ ሁ ያስተማሩት ልጃቸው የሞያ ውጤት ምግባቸውን አለመለየቱ ሌላ የሁለት ጓዳ የሚጋባ የእውነት ስሜት ነው አኔ ብሆን የሚያሰኝ እና እንዴት የሚያስብል ነው የወንድ ልጅ ፈተናው በሁለት ጓዳ ዝግጅት ።
ይህ ዝግጅት መልከ ብዙ ነው የእናት ፍቅር ፣ የሚስት ክብር የወንድ ልጅ ኩራት እና ፍቅሩ ጭምር የሚፈተንበት ነው ይህ ሁሉ ያለው በሁለት ጓዳ ነው ጎራ ይበሉ ይቅመሱት ይወዱታል ፣ ሁለት ጓዳ ።
#2ጓዳ ዘወትር ረቡዕ ከምሽቱ 3፡00 በ #አቦልቲቪ ፣ ዲኤስቲቪ ቻናል 465 ይጀምራል!
በ #MyDStv አፕ አሁን አገልግሎቱን ያስቀጥሉ: https://tinyurl.com/yc8p3xvd እና በ DStv Stream App የሚወዱትን የአቦል ቲቪ ድራማዎች ይመልከቱ፡ http://tinyurl.com/bdh2j9ed