ፍቅር፣ ኮሜዲ፣ አክሽን፣ ሪያሊቲ እና ድራማ - አቦል ጋር ሁሉም አለ። እናንተ የሚጠበቅባችሁ መጠየቅ ብቻ ነው። የፍቅረኞች ወር ለጥንዶች ብቻ አይደለም፣ ለቤተሰብ፣ ለጓደኞች እና ከሁሉም በላይ ደግሞ ለድራማ ያለንን ፍቅር የምናጣጥምበት ወር ጭምር ነው። በፍቅረኞች ወር እንዚህን ምርጥ ድራማዎች መመልከት ይችላሉ!
የእሳት እራት
ፍቅር እና ጥላቻ በቀጭን መስመር እንደሚለያዩ የሚያሳየን ምርጥ ድራማ። ግዛቸው የአዲናን ህይወት ስቃይ ብቻ ለማድረግ የሚያደርገው ጥረት እየተሳካለት ነው። አዲና የቅርብ ጓደኞቿን እና የልጅነት ጓደኞቿን አጥታ ብቻዋን ቀርታለች። ግዛቸው ለምን ይሄን ያህል እንደቀረባት በዜና ሲጠየቅ መልሱ አጠራጣሪ ነው። አዲናን የእውነት አፍቅሯት እና ሊያገባት ፈልጎ ሊሆን አይችልም፣ ነገር ግን እርሱ እንደሚለው ፍቅር እና ጥላቻ በቀጭን መስመር ነው የሚለያዩት። የእሳት እራት ዘወትር ከሰኞ - አርብ ከምሽቱ 2:30 በአቦል ቲቪ፣ ዲኤስቲቪ ቻናል 464 እንዳያመልጥዎ!
አሻራ
ትዝታ ዘአላዛር ላይ ከማርቆስ ጋር እንደማገጠችው ማርቆስ በእሷ የማገጠ ሲመስላት በጣም ትናደዳለች። እውነት ባይሆንም አላዛር የዛኔ የተሰማውን ስሜት ለትንሽ ጊዜ ሲሰማት በአደረገችው ነገር የምትቆጭ ከሆነ ለማየት እየተጠባበቅን ነው። አላዛር ያለፈው ህይወቱን ለማስታወስ እያደረገ ያለው ጥረት በቅርብ የሚሳካ ይመስላል። በቀጣይ በአሻራ የሚፈጠረውን ለማየት ዘወትር ከሰኞ - ረቡዕ ከምሽቱ 2፡00 በአቦል ቲቪ፣ ዲኤስቲቪ ቻናል 465 ይከታተሉት።
ሰራተኛ ፈልጉልን
ሱዚ እና ዜና በምዕራፍ 2 ተመልሰው መጥተዋል እናም ከባለፈው በላይ አስቂኝ ክስተቶችን መጠበቅ እንችላለን። ሱዚ በመጨረሻ እንደፈለገችው አርግዛለች እናም ቤተሰባቸው እያደገ ነው። ነገር ግን በቤታቸው እንደጠበቁት ሁሉም ሰላም አይደለም፣ የሱዚ ልዩ የምግብ ህጎች እና እንደ ድመት እና ውሻ የሚጣሉት ሰራተኞች እያዝናኑን ነው። ሰራተኛ ፈልጉልን ዘወትር ሀሙስ ከምሽቱ 3፡00 በአቦል ቲቪ፣ ዲኤስቲቪ ቻናል 465 ይከታተሉት!
ስፍራሽ ብዙ
ተማሪዎቹ አሁን ተላምደው ወደ ጓደኝነት እያመሩ ነው። ስፍራሽ ብዙ የሚጠቀሙትን ዜዴ መረዳት ባይችሉም ባህሪያቸው ቀስ በቀስ እየተሻሻለ ነው። ነገር ግን ይህ ማለት ጨዋ ሆነዋል ማለት አይደለም። ይልቁን በቡድን ሆነው ከቤቱ እንዴት እንደሚወጡ ያቅዳሉ። የባለፈው ሳምንት ሙከራቸው አልተሳካም፣ በእዚህ ሳምንት የሚሞክሩትን ዘዴ ይከታተሉት። ስፍራሽ ብዙ ዘወትር ሀሙስ ከምሽቱ 2፡00 በአቦል ቲቪ፣ ዲኤስቲቪ ቻናል 465 እንዳያመልጥዎ!
ድንቅነሽ
መልከ መልካም ባለመሆኗ ከልጅነቷ ጀምሮ ስትገፋ የኖረችው ውብዓለም ከስኬታማው የቲያትር ድራማ ድንቅነሽ ምረቃ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ለቃለ መጠይቅ ትቀርባለች። ስኬቷን የምታጣጥምበት ደስተኛ ጊዜ መሆን የነበረበት ጊዜዋ ግን በጠላቶቿ ተጠምዷል። የውብዓለምን ልዩ ታሪክ ዘወትር አርብ ከምሽቱ 2፡00 በአቦል ቲቪ፣ ዲኤስቲቪ ቻናል 465 ይከታተሉት!።
ሁለት ጓዳ
አዲሱ የአቦል ቲቪ የምግብ አሰራር ውድድር ልዩ ይዘት ይዞ ቀርቧል። እናት ወይስ ሚስት? ዳኛው የእናቱን እና የሚስቱን ምግብ ቀምሶ የሚበልጠውን መምረጥ ይኖርበታል። ውድድሩ ልብ አንጠልጣይ ነው። ሁለት ጓዳ ዘወትር ረቡዕ ከምሽቱ 3፡00 በአቦል ቲቪ፣ ዲኤስቲቪ ቻናል 465 እንዳያመልጥዎ!
ከእነዚህ ምርጥ ድራማዎች እየመረጣችሁ የፍቅረኛሞችን ወር እየተዝናናችሁ ማሳለፍ ትችላላችሁ!
በ #MyDStv አፕ አሁን አገልግሎቱን ያስቀጥሉ: https://tinyurl.com/yc8p3xvd እና በ DStv Stream App የሚወዱትን የአቦል ቲቪ ድራማዎች ይመልከቱ፡ http://tinyurl.com/bdh2j9ed