Logo

የስፍራሽ ብዙ ገፀ ባህሪያት

ዜና
31 ጃንዩወሪ 2025
ግብረገብነት ለሀገር ሁለተናዊ እድገት እና ትውልድን ሀገር ወዳድ ሆነው እንዲያድጉ ለማድረግ ወሳኝ ነው።
Sifrash bizu

የባህሪ መገራት ለጠንካራ ችግር ፈቺ ትውልድ መፈጠር ትልቅ አስተዋፅኦ አለው።

በተማሪዎች መካከል የሚኖር መስተጋብር ለነገ ሀገር ዋስትና የመሆኑ ነገር እሙን ነው። በዚህ ረገድ ክፍተት መኖሩ ያረጋገጠው የሀገሪቱ ትምህርት ሚንስትር ከመደበኛ ትምህርት ባሻገር የግብረገብ ትምህርት በስርአተ ትምህርቱ መካተት እንዳለበት አምኗ። ሆኖም ግን ይህን ሃሳብ የትውልድ ማዳን ተልዕኮ የሚወጣ በሃላፊነት የሚሰራ ልምድ ያለው ሰው ግድ ነው።

አነሆ በዚህ አዙሪት ውስጥ ሳለ ትምህርት ሚንስትር አንድ ሰው ያገኛል። በስልሳዎቹ የግብረገብ መምህር የነበሩ ልምድ ከእውቀት ያዳበሩ ሀገር የሚወዱ የትውልዱ ክፍተት የሚከነክናቸው ለዚህም መስራት ፍላጎት ያላቸውን ስፍራሽ ብዙ የተባሉ ግለሰብን አግኝቷል። ተፈላጊ እና ፈላጊ ሲገናኙ ማለት ይህ ነው።

ስፍራሽ ብዙ ልምድ እና እውቀት ብቻ አይደለም ያላቸው። የሀገር ፍቅር እና ፍላጎት ጭምር የከበባቸው የመርህ ሰው ናችው። እሳቸው የተሰጣቸው ሃላፊነት ለመጀመር ከውስን ተማሪዎች ጋር ለመቆየት በማሰብ ከሰባት ያላነሱ ልዩ ልዩ እና ባህሪ የስነምግባር ጉድለት ያለባቸውን ተማሪዎች ይዘው ወደ ስራ ገብተዋል ።

ሳባ

ሳባ አንባቢ ናት ነገር ግን ማንበብ ያልቀየራት ማስመሰል የሚዋጣላት ሁሉንም አዋቂ ነኝ ባይ መምህር የምታሸማቅቅ አይነት ተማሪ ናት። ስም በማጠልሽትም ትታወቃለች። ይህን አብሯት የኖረ ባህሪ ስፍራሽ ብዙ ትገራው ይሆን?

ከስፍራሽ ብዙ የምንረዳው ይሆናል።

ሄለን

ሄለን ሌላኛዋ የባህሪ ጉድለት ያለባት ተማሪ ናት። ሄለን በእጅ አመል ትታማለቸሰ። እሷ ባለችበት ሁሉ አንዳች ነገር ይሰወራል። በዚህም በአካባቢዋ ላይ ያሉ ሁሉ በጥርጣሬ ነው የሚመለከቷት። ከዚህ ውጪ ሌሎች ተማሪዎች እርስ በእርሳቸው መተማመን መኖር የለበትም በሚል ጥርጣሬ ውስጥ ይሆኑ ዘንድ አበክራ ትሰራለች።

ሄለን እንዴት መስመር ትይዛለች? ስፍራሽ ብዙ ለዚህ መልስ አታጣም።

ቅድስት

ቅድስት እኩይ ተግባር ላይ የበረታች ራስ ወዳድ ነች። ለዚህ አመሏ ደግሞ ብልጣብልጥነት ታበዛለች። በተማሪዎች እና በመምህራን መካከል ፀብ አጫሪ ናት። ብዙ ክሶች አሉባት። ተማሪዎች ተስማምተው ስታይ አይኗ ይቀላል። በአጭሩ የፀብ ደላላ ናት ማለት ይቻላል። ስፍራሽ ብዙ ለቅድስት ባህሪም መፍትሄ አላት! የሚሆነውን ለማየት የስፍራሽ ብዙ ድራማን ይከታተላሉ።

ማርሲላስ

ማርሲላስ ውብ እና ራሷን የቆንጆ ልክ ነኝ ብላ ስለምታምን በትምህርት ቤት ያልተገባ አለባበስ ታዘወትራለች። ሌላ የእሷ መጥፎ ባህሪ በእድሜ ከሚበልጣት ተማሪ ጋር ስትባልግ ተይዛለች። ይህ ደግሞ ከባድ የባህሪ ጥሰት ነው። በመታረም ሂደት ውስጥ ምን ይፈጠር ይሆን?

ሰላም

ሰላም ደግሞ ሃሳብ እና የኔ የምትለው አንዳች አቋም የላትም። በጓደኞቿ የምትመራ ናት ነገር ግን በትምህርት ውስጥ በመደባደብ ስመጥር ናት። በቅጥር ግቢ ውስጥ አልኮል በመጠጣት ትከሰሳለች። ስፍራሽ ብዙ እንዴት ትገራታለች? ድራማውን በመከታተል እንመልከት።

ረቂቅ

ሱስ ያዳከማት በተደጋጋሚ ክስ የሚቀርብባት ነገሮች በተለይም ያልተገቡ አመሎቿን በድብቅ የምትከውን መሳቅ መጫወት የምትወድ በመምህራን ላይ የምታሾፍ ለሁሉም መምህር ቅፅል ስም የምትሰጥ ጨዋ መሳይ ክፉ ናት።

ልዩ

ልዩ ደግሞ ስምን መልአክ ያወጣዋል ይሉ እንደ ስሟ ከሁሉም የምትለይ ተማሪ ናት። በዚህ ባህሪዋ ግን ተማሪዎች በጥርጣሬ ነው የሚያዩዋት። ሰላይ ናትም ይሏታል። ስለ ልዩ፣ ልዩ ባህሪ ማወቅ ይፈልጋሉ? እነሆ በዚህ መልኩ የሚቀጥል ድንቅ ድራማ ስፍራሽ ብዙ አቅርበናል።

#ስፍራሽ ብዙ ዘወትር ሐሙስ ምሽት 2:00 በ #አቦልቲቪ፣ ዲኤስቲቪ ቻናል 465 ይቀርባል!

በ #MyDStv አፕ አሁን አገልግሎቱን ያስቀጥሉ: https://tinyurl.com/yc8p3xvd እና በ DStv Stream App የሚወዱትን የአቦል ቲቪ ድራማዎች ይመልከቱ፡ http://tinyurl.com/bdh2j9ed