Logo

በአንድ የስዕል ኤግዚቢሽን የሚጀምር የህይወት አጋጣሚን የሚተርክ ምህረት ድራማ ።

ዜና
27 ዲሴምበር 2024
ምህረት ድራማ በአንድ የስዕል ኤግዚቢሽን ላይ በሚጀምር አጋጣሚን የሚተርክ- ምህረት ድራማ ።
Mihret S1

ምህረት ድራማ በአንድ የስዕል ኤግዚቢሽን ላይ በሚጀምር የትውውቅ አጋጣሚ ታጅቦ ምህረት እና አማን በተባሉ ወጣቶች የፍላጎት እና የሃሳብ ግጭትን ያሳያል። በሰው ህይወት ውስጥ የሚከሰቱ የማይገመቱ እና መልከ ብዙ ጉራማይሌ ነገሮችን እያጣቀሰ ምህረት ድራማ በልዩ ክስተት ታጅቦ ይቀርብልናል።


ምህረት ለጓደኛዋ እና እህቷ የአማንን ደግነትን የስዕል ኤግዚቢሽን ለማዘጋጀት እንደሚረዳት ስለነገረቻቸው ደስተኛ መሆናቸውን ይገልፁላታል።
በዚህ የህይወት ውጣውረድ በግልጽ የሚያሳይ ምህረት የተሰኘ አዲሱ ድራማ የአማን ወላጅ አባቱ በህክምና ሊድን በማይችል በሽታ እየተሰቃዩ ያሉ ሰው ሲሆኑ ከዚ ቀደም በህይወታቸው ውስጥ በገጠማቸው የተለየ ክስተት በመነሳት ቀደምት ሀገራዊ  ጥበብ በሆነው የጠልሰም ጥበብ ተጠቅመው ከህመማቸው ሊፈወሱ እንደሚችሉ አምነዋል።


ለዚህም ደሞ ልጃቸው አማንን ይሄን ጥበብ ሊሰራ የሚችል ሰው ሊያመጣላቸው እንደሚገባ አሳምነውታል። አማንም የገባበት ገብቶ ይሄን ጥበብ መስራት የሚችል ሰው አግኝቶ እንደሚያድናቸው ቃል ገብቷል። ይህን አላማ በመሰነቅ በተለያየ ጊዜና ሰበብ የዚህን ጥበብ ባለቤቶች ለማግኘት የሞት ሽረት ትግል ሲያደርግ የቆየ ሲሆን በአንድ አጋጣሚ ይህንን ተልዕኮ ልታሳካ የምትችል  የፍላጎት ጥማትን የምታረካ ሴት ያገኛል። ይህ አጋጣሚ ለዚህ ሰው የዘመኑ ስኬት የአደራው ምላሽ ይሆን ወይ በሚል በልበ ስቀሳ ውስጥ ሳለ ነበር ምህረትን የሚያገኛት።


በሁለት ፍላጎቶች መሀል የተወጠረው አማን ከጊዜ ወደ ጊዜ ለምህረት  ፍቅሩን የሚገልጽበት መንገድ ያልተለመደና አስጨናቂና ይሆንባታል። የሚያሳየው የባህሪ ለውጥ  ምህረትን ይረብሻታል። ነገሮችን በተሻለ እና በተረጋጋ መንገድ እንዲያስኬድ ብትሞክርም ሊሳካላት አልቻለም። ሁኔታዎቹ ከልክ እያለፉ እና እየከረሩ መጥተው አንድ ቀን ምሽት እንደ  ቤተሰቧ ከምታየው አብርሀም ጋር እንደማገጠች በማሰቡ ምክንያት እጁን ያሳርፍባታል።


በደረሰባት ጥቃት አነስተኛ  የስነልቦና ቀውስ ውስጥ የቆየችው ምህረት በእህቷ ሰናይት እንዲሁም አብርሀም እና  በዶክተር ሳሙኤል እርዳታ ወደ ሰላማዊ እና ደስተኛው ማንነቷ እንድትመለስ ጥረት ሲደረግ የቆየ በመሆኑ በመጠኑ ተረጋገታ ወደምትወደው የስዕል ሙያዋ ትመለሳለች።
አብርሀም ጉዳዩን በጥልቀት ስለሚያውቅ አማንን ተከታትሎ ለማያዳግም ፍርድ ለማቅረብ ሲታገል፣ እህቷ ሰናይት ምህረትን ለመታደግ ከህግ ውጭ የሆኑ ሌሎች አማራጮችን በድፍረት ስትሞክር ሁኔታው እየተካረረ ይሄዳል።
ምህረት ድራማ የህይወት መንገድ ነው። የፍቅር፣ የባህሪ ልዩነት እና ለአባት የሚከፈል መስዋዕትነትን ማሳያ አድርጎ ልዩ ፈርጅን እና እውነታን ፍንትው አድርጎ ያሳያል።


በተጨማሪም ምህረት ድራማ ህይወት የማይገመት የቅፅበት ውሳኔ እና አጋጣሚ የሚቀይራት ትንሽ ስህተት ትልቅ ናዳ የምታመጣ በሳል ውሳኔ የምትፈልግ የብልህ መንገድ መሆኗን ያሳየናል። ለውሳኔ ማሰላሰል፣ ለሃሳብ መጨነቅ ሳይሆን መፍትሔ መፈለግ፣ በስሜት ሳይሆን በምክንያት ህይወት መምራት እንደሚያስፈልግ የሚጠቁም ሁነኛ ድራማ ነው ምህረት ድራማ

# ምህረት ዘወትር ሰኞ ከምሽቱ 3:00 #አቦልቲቪ ዲኤስቲቪ ቻናል 465 ይቀርባል!

 #MyDStv አፕ አሁን አገልግሎቱን ያስቀጥሉhttps://tinyurl.com/yc8p3xvd እና  DStv Stream App የሚወዱትን የአቦል ቲቪ ድራማዎች ይመልከቱ፡ http://tinyurl.com/bdh2j9ed