የእሳት እራት ልብ አንጠልጣይ ድራማ በአስገራሚ ታሪኩ ሀሳባችንን ሰርቆታል። ድራማው የአዲና እና ሌሎች ባላጠፉት ጥፋት እየተቀጡ ያሉ ገጸ ባህሪዎች ታሪክ ላይ ያተኩራል ነገር ግን የእነዚህ ገጸ ባህሪዎችን ህይወት የሚቆጣጠሩ ጨካኝ ሰዎች አሉ። እነዚህም ዜና እና ግዛቸው ናቸው።
እነዚህን ጨካኝ ሰዎች የሚያመሳስላቸው እና የሚያለያያቸው ወሳኝ ነገሮች አሉ።
- ዜና
ዜና ሁሉንም ሰው በቁጥጥሩ ማዋል የሚፈልግ፣ ለሰው ህይወት ክብር የሌለው እና ሀብት እና ዝናው ምንም ወንጀል ቢፈጽም እንደሚከላከለው እርግጠኛ ነው። ዜና በብዛት የሚያተኩርባቸው ሰዎች መስታወት እና ሚስቱ ትሁት ናቸው። መስታወትን ስለእሷ በሚያውቀው መረጃ እያስፈራራ እንደንብረቱ ይቆጥራታል፣ በተጨማሪም እያንገላታት ከምታፈቅረው ሰው ጋር እንዳትሆን ይከለክላታል። ትሁትን ደግሞ የእራሷ ህይወት እና ሀሳብ እንዳይኖራት ከልጆቿ ጋር ይለያታል እናም ይደበድባታል።
የዜና ባህሪ እንደሚያሳየው ከሆነ፣ የዜና ደካማ ጎን ልጆቹ ብቻ ናቻው። ዜና ሌሎች ሰዎችን ጨክኖ የሚጎዳቸው በሀይሉ ከምስከሩ የተነሳ ሌሎች ሰዎች የእሱ አይነት ሀይል ስለሌላቸው አይነኩኝም ብሎ ስለሚያስብ ነው። ነገር ግን እስካሁን መስታወትን አስገድዶ እንድታገኛቸው ያደረጋቸው ባለስልጣኖች ትኩረታቸውን ወደ መጀመሪያ ልጁ አዙረዋል። ዜና እውነተኛ ደካማነት ሲያጋጥመው ምን አይነት እርምጃ ይወስድ ይሆን?
- ግዛቸው
ግዛቸው በጉልበቱ የሚተማመን፣ አንድን ሰው ከጠላ ችክ ብሎ የሚይዝ እና ለሰው ህይወት የማይራራ ሰው ነው። በአዲና እገታ እና ሞት ምክንያት ታስሮ ለ3 አመት ስለቆየ አዲናን ለመበቀል ተነስቷል። አዲናን ስለመበቀል ብቻ ከማሰቡ የተነሳ በአካባቢው ያሉት የሚወዱት ቤተሰቦቹን ሲያጣ እራሱ አያቆምም። ይልቁን የእነሱንም ጉዳት የአዲና ጥፋት አድርጎ ይበልጥ በበቀሉ ይተማመናል።
የእንደዚህ አይነትን ሰው ሀሳብ መቀየር እጮኛው እንዳየችው የማይቻል ነገር ነው። አንድ ጊዜ እራሱን ከጥፋተኝነት ነፃ አድርጎ ተበድያለው የሚል አስተሳሰቡን አይለቀውም። የእራሱ ጥፋት የሆኑትንም ነገሮች በእሷ አላኮ አጠገቡ የነበሩት ሰዎች ትተውት ሲሄዱም በቀሉን መርሳት አልቻለም። አዲናን ንጉሱ ሆኖ ቀርቧት ሲያውቃት ጥፋተኛ አይደለችም ብሎ ማመን ይችል ይሆን?
የእሳት እራትን ዘወትር ከሰኞ - አርብ ከምሽቱ 2:30 በአቦል ቲቪ፣ ዲኤስቲቪ ቻናል 465 ይከታተሉት!