Logo
Yesat Erat S1

ንጉስ እና ግዛቸው፡ የበቀል ሁለት መልኮች

ዜና
09 ዲሴምበር 2024
ግዛቸው አዲናን ሊበቀላት የሚያደርገው ዝግጅት ወደሚቀጥለው ደረጃ ይሄዳል።
yesat erat revenge article

ግዛቸው ውስብስብ ገጸ ባህሪ አለው። ለሚወደው ሰው ሲሆን አለምን በአንድ አግሯ አቁሞ የሚፈልጉት ነገር እንዲያገኙ ከማድረግ ወደ ኋላ አይልም። ነገር ግን አንድን ሰው ሲጠላ ያንን ሰው ሊጎዳ እራሱን እና አለምን በእሳት ከማንደድ ወደ ኋላ አይልም። አሁን የግዛቸው ጥላቻ ያተኮረባት አዲና ነች።

አዲና በግዛቸው ዘመድ በልሁ ተጠልፋ የግዛቸው ማረፊያ ቤት በበልሁ ተወስዳ ነበር በዚህ መሀል ግዛቸው ሳያስበው የወንጀሉ አጋዥ ይሆናል። ፖሊሶች አዲናን እሱ የሚቆይበት ቤት አግኝተዋት እናም ሞታለች ተብሎ ሲታመን፣ ግዛቸው ባልፈጸመው ወንጀል ምክንያት ለ3 አመት ይታሰራል። በዚህም ጊዜ የሚወዳት እጮኛው ትታው ትሄዳለች። ግን ግዛቸው ጥላቻው እዚህ ሁሉ ጣጣ ውስጥ ላስገባው ዘመዱ በልሁ ሳይሆን፣ ያለጥፋቷ ለታገተችው አዲና ነበር።

አዲና ሞታለች ተብሎ በመታመኑ የግዛቸው ጥላቻ ማረፊያ አልነበረውም፣ ነገር ግን ከ7 አመት በኋላ አዲና ከገዳም ተመልሳ ስትመጣ የግዛቸው ጥላቻ አድጎ ነበር የጠበቃት። ቤተሰቧን ከ7 አመት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ አግኝታ ደስታዋን ሳትጨርስ፣ የበልሁ እና ግዛቸው በቀል ዒላማ ትሆናለች። ጥፋቱን መቀበል የማይፈልገው በልሁ እና በአዲና ተበድያለሁ ብሎ የሚያምነው ግዛቸው ህይወቷ ለማበላሸት ይነሳል። በዚህ በቀል ምክንያት ግን የአዲና ወንድም ዘሬ እና የግዛቸው ወንድም ገረመው ህይወታቸውን ያጣሉ ነገር ግን ግዛቸው የሚወደው ወንድሙን ማጣቱ እንኳን አላስቆመውም። ይልቁን የወንድሙ ሞት ምክንያት ነች ብሎ ያምናል።

ግዛቸው በቀሉን በመቀጠሉ ግን ያልተወለደውን ልጁን እና እጮኛውን ያጣል። ማንኛውም ሰው ይህ በቀል ማቆም አለብኝ ብሎ እነዚህን ምልክቶችን ሊሰማ ይችላል ነገር ግን ግዛቸው እንደዚህ አላደረገም። ግዛቸው በህይወቱ ውስጥ የቀረው ነገር ለአዲና ያለው ጥላቻ ብቻ ነው ስለዚህ የህይወቱን ባዶነት እና ሀዘኑን አፍኖ አዲናን ለመበቀል ሙሉ ለሙሉ ማንነቱን ይሰጣል።

ከግዛቸው ጥላቻ ይባስ ብሎ ንጉስ ይመጣል። ንጉስ አንድ እና አንድ አላማ ብቻ ነው ያለው ያ አላማም አዲናን ማሰቃየት። በቀል በሆነ ጊዜ ነፍሰ ጡር እጮኛ ፣ ጤናማ ወንድም እና ደስተኛ ህይወት የነበረውን ሰው ወዙ የጠፋ ቀፎ ይቀይረዋል። የንጉስ በቀል ገና መጀመሩ ነው ነገር ግን ንጉስ በቀሉን ቢያሳካው ወደ ድሮ ማንነቱ መመለስ ይችል ይሆን?

Yesat Erat S1 POLL
Yesat erat s1 poll 7

በበቀሉ ደሰተኛ የሚሆን ይመስልዎታል?

አዎ በቀሉ ያስደስተዋል 100%
አይ አያስደስተውም፣ ህይወቱ ባዶ መሆኑን ነው የሚያስታውሰው።0%

የንጉስ እና አዲናን ታሪክ በየእሳት እራት ዘወትር ከሰኞ - አርብ ከምሽቱ 2:30 በአቦል ቲቪ ፣ ዲኤስቲቪ ቻናል ይከታተሉት!