ባዩሽ ከበደ፣ አማኑኤል የሺዎንድ እናም ሌሎች ተወዳጅ አርቲስቶችን ይዞ የሚቀርበው ምርጥ ብርሃን የተሰኘው ድራማ በአቦል ቲቪ ሲያዝናናን እና ሲያስተምረን ቆይቷል። ድራማው ብርሃን የተባለች የስነልቦና ህክምና የምትሰጥ የህክምና ባለሞያ ታካሚዎቿን እንዴት እንደምትረዳ ያስቃኘናል። ብርሃን ለተለያዩ ታካሚዎች ከምትሰጣቸው ምክሮች እና የመረጋጊያ ዘዴዎች እኛንም ተምረናል።
ከእነዚህ ትምህርቶች በጣም የጠቀሙን እነዚህ ናቸው፦
- ሱስ ማቆሚያ ዘዴዎች
ብርሃን በመጀመሪያ ሱሰኛ ታካሚዎቿ አደንዛዥ እፅ እንዲጠቀሙ የሚገፋፉቸውን ምክንያቶች ትደርስባችዋለች። ችግሩ ሳይታወቅ መፍትሄ ማግኘት አይቻልም። በቀጣይ በቡድን ቴራፒ ታካሚዎች እርስበርሳቸው እንዲደጋገፉ እና የመጠቀም ፍላጎታቸውን በሌላ ድርጊት እንዲተኩት ትመክራቸዋለች። ይህ ለሱስ ብቻ ሳይሆን ማንኛውንም መጥፎ ባህሪ ለመቀየር የሚረዳ ምክር ነው።
- የብቸኝነት እና ፍርሃት ስሜት ምክንያቶች
ማሪያ በአካባቢዋ ያሉትን ሰዎች እንድትሸሽ እና ማውራት እንዲያቅታት የሚያደርጋት ፍራቻ በልጅነቷ አድሮባታል። ማሪያ የሚሰማት ስሜት የተፈጠረባት ካለፉት ብዙ አስፈሪ አጋጣሚዎች ነው። እናም ከዚህ የተነሳ እራሷን ለመከላከል ብላ የለመደቻቸው ባህሪዎች አሁን እንቅፋት ሆነውባታል። ይህ የስነልቦና ችግር ማህበራዊ ቀውስ ይባላል። ብርሃን ይሄን ችግር ለማለፍ ለማሪያ የመከረቻት ምክር ለማንኛውም ሰው በአስጨናቂ ጊዜ ላይ የሚረዳ ነው። አይናችንን ጨፍነን ደስ የሚል ቦታ እናስባለን፣ ሰላም የሚሰጠን አምላክ እና ሰው አብሮን አለ። እዚህ ቦታ ትልቅ ሳጥን አለ፣ ሁሌም የሚረብሹንን ሀሳቦች እና ትዝታዎችን ሳጥኑ ውስጥ ከተን ሳጥኑን እንዘጋዋለን። ሳጥኑን ቆልፈን ቁልፉን ሳጥኑ ስር እናስቀምጠዋልውን፣ ካለኛ ፍቃድ ማንም ይሄን ሳጥን መክፈት አይችልም። ይሄን ካደረግን በኋላ አይናችንን ገልጠን ስሜታችንን እናረጋጋለን።
- የማንፈልገውን ነገር እንዴት እንደምንጋፈጥ
የብርሃን የመጀመሪያ ታካሚ አለም ካለፍቃዷ ማንነቷን የሚያጋልጥ ቪዲዮ በማህበራዊ ሚዲያ ተለቆ ወደ ቀውስ አስገብቷታል። ከዚህ አልፎ ደግሞ ትልቁ ፍራቻዋ እውነቱን ለሚደግፋት እና ለሚወዳት ሰው ተናግራ ብቻዋን መቅረት ነበር። እውነቱን በማጋለጥ ከሚስጥር ውስጥ ወጥታ እንዴት ወደፊት መሄድ እንደምትችል መወሰን ትችላለች። ይሄን ማድረግ ግን በጣም ከባድ ነገር ነ። ስለዚህ ብርሃን የሚረዳት ምክር ሰጥታታለች። መጀመሪያ ሁለቱንም ምርጫዎቿን (መናገር ወይም አለመናገር) በደንብ አስባባቸው፣ የሁለቱም ውጤት ምን ሊሆን እንደሚችል መረዳት መቻል ነው። ከዚህም በኋላ አንዱን ምርጫ ነው ብላ ላመኘችበት መርጣ ወዲፊት ማንነቷ ደብዳቤ መጻፍ እና ምርጫዋን ማድረግ።
ብርሃን በተለያዩ ታሪኮች እያዝናና ጠቃሚ ትምህርቶችን አስተምሮናል! የሚቀጥሉትን ክፍሎች ዘወትር ሰኞ ከምሽቱ 3:30 በአቦል ቲቪ፣ ዲኤስቲቪ ቻናል 465 ይከታተሉት!
በ #MyDStv አፕ አሁን አገልግሎቱን ያስቀጥሉ: https://tinyurl.com/yc8p3xvd እና በ DStv
Stream App የሚወዱትን የአቦል ቲቪ ድራማዎች ይመልከቱ፡ http://tinyurl.com/bdh2j9ed