Logo
alawkim s1

አላውቅም አናውቅም ላይ የተነሱ 3 ትልቅ ርዕሶች

ዜና
19 ዲሴምበር 2024
የአላውቅም አናውቅም ቡድን በጭንቅ አዋላጅነት ሲሰሩ የገጠሟቸው ትላልቅ ትምህርቶች እነዚህ ነበሩ።
alawkim anawkem article

አላውቅም አናውቅም ሮዳ፣ ሊያት እና አመቴ በጭንቅ አዋላጅነት ሞያቸው የሚያጋጥሟቸውን ልዩ ልዩ ክስተቶች እና ቤተሰቦች ይዞልን ቀርቧል። በዚህ ሳምንት የሚቀርበው የመጨረሻውን ክፍል በማስመልከት እነዚህ ልዩ ክስተቶች ያስተማሩን ትልቅ ትምህርት ይበልጥ እንወያይበታለን

  1. የአጋርን አስፈሪ ባህሪዎች

ታሪካችን በተለያዩ ቤተሰቦች ላይ ከማተኮሩ በፊት የሮዳን ትዳር እና ያለፈው ባለቤቷ ምን አይነት ሰው እንደሆነው አጉልቶ አሳይቶን ነበር። ሮዳ ከታዴ ጋር የነበራት ትዳር ከርቀት ሲታይ ደስተኛ እና ፍቅር የበዛበት ቢመስልም፣ ቀረብ ተብሎ ሲታይ ግን የሚያስጠላው እውነት ይጋለጣል። በታዴ ሞት ምክንያት ደስተኛ የሆነችው ሊያት ቀድማ እንዳየችው፣ ታዴ ሮዳን በእጁ ካስገባ በኋላ ህይወቷ ውስጥ ካሉት ሰዎች ጋር፣ ከቤተሰቦቿ ጋር እና በጠቅላላ ከውጭው አለም ጋር ነው ያቆራረጣት። ሮዳ ይሄንን ለመበቀበል ቢከብዳትም፣ ታዴ ጥሩ ባል እንዳልነበረ እና ፍቅር ሳይሆን ተቆጣጣሪነት እንደሚሰማው አይተናል። በሮዳ ታሪክ የተማርነው፣ ለአንድ ሰው ፍቅር ተብሎ የተሟላ ህይወትን መኖር ማቆም ወደ አስከፊ ህይወት እንደሚመራ ነው።

  1. ከቤተሰብ እርዳታ መቀበል

አያንቱ እና መረድ በእናቶቻቸው ጣልቃ ገብነት ተጨንቀው የጭንቅ አዋሎጆቹን ይቀጥሯቸዋል። ወድያውኑ ግልጽ የሆነው አያንቱ እና መረድ የእንክብካቤ ማነስ ኖሯቸው ሳይሆን ከእናቶቿቸው የሚያስጥላቸው ሰው ፈልገው ነው። ሮዳ ደንበኞቿን ደስተኛ ለማድረግ እንደጠየቁት ሆቴል ሂደው እንዲታረሱ ታመቻችላቸዋለች ነገር ግን ጥንዶቹ በመጀመሪያ በዚህ ደስተኛ ቢሆኑም ወዲያውኑ ብቸኝነት እንዳሰቡት አሪፍ እንዳልሆነ ይረዳሉ። በመጨረሻው ሰዓት ላይም ከእናቶቻቸው ጋር በመታረቅ እርዳታቸውን መቀበል ይጀምራሉ። ከአያንቱ እና መረድ የተማርነው፣ ቤተሰባችን አንድአንዴ የምንፈልገውን መረዳት ሊያቅተው ይችላል ነገር ግን በመነጋገር መፍታት ነው እንጂ እራስን ማግለል መፍትሄ እንዳልሆነ ነው።

  1. የእህት ቅናት መንስኤ

ምዕራፍ እና ሰውበቃ የጭንቅ አዋላጆቹን የቀጠሯቸው ለአራስ ልጅ እርዳታ ፈልገው ሳይሆን፣ ታላቅ እህቱ ጣፋጭን ከእሱ አጠገብ ለማራቅ ነው። ጣፋጭ ከወንድሟ እንድትርቅ የተፈለገበት ምክንያት ደግሞ ወላጆቿቸው ጣፋጭ ያላትን ቅናት መቋቋም አቅቷቸው ነው። ነገር ግን የጭንቅ አዋላጆቹ ችግሩን ለመፍታት የተጠቀሙት መንገድ ለየት ያለ ነበር፣ ችግሩ የመጣው ከወላጆች እንጂ ከጣፋጭ አልነበረም። ወላጆቿ ጣፋጭን በመዋሸት፣ በማባበል እና ወንድሟን እንደምትጎዳ አድርገው በማየታቸው ጣፋጭን እየተረሳች እንደሆነ እንዲሰማት አድርገዋታል። በእዚህ ክፍል የተማርነው፣ ልጆችን በማታለል ችግር መፍታት እንደማይቻል እና ልጆችን ክብር እንደሚገባቸው አይነት ሰዎች አድርጎ በማየት ዋናው ችግር መፍታት እንደሚቻል ነው።

 

እኛ የወደድናቸው የአላውቅም አናውቅም ትምህርቶች እነዚህ ነበሩ እርስዎ የትኛውን ታሪክ ወደውታል? በማህበራዊ ሚዲያ ገፆቻችን ኮሜንት በማድረግ ያሳውቁን!

የመጨረሻው የአላውቅም አናውቅም ክፍል ሀሙስ ከምሽቱ 2፡00 በአቦል ቲቪ ፣ ዲኤስቲቪ ቻናል 465 እንዳያመልጥዎ!