ልዩ ጭንቅላት ያለው ተመራማሪ እና አገሩን ለመጥቀም መስዋትነት የሚከፍል ጀግና ነው! ከሃያ ዓመታት በፊት አንድ የመንግስት ድጋፍ ያለው ነገር ግን ሚስጥራዊ ክፉ ዓላማ የነበረው የሳይንሳዊ ምርምር ፕሮጀክት ስኬታማ ግኝት አስገኘ። መሪዎቹ ዘሪሁን፣ አፈወርቅ እና ዮሴፍ ድብቅ አላማቻውን ያወቀውን ቁልፍ ሰራተኛ አቤልን ለማስወገድ ወሰኑ። አቤል በባልድረቦቹ በተደረገ አሻጥር፣ የምርምር ቡድኑ አባል በሆነችው የሴት ጓደኛው ሳባ በጥይት ተመቶ ቢወድቅም ህይወቱ ግን አላለፈችም። ባልደረቦቹ የሞተ ቢመስላቸውም በገጠራማ አካባቢ ተደብቆ ኖረ። አሁን ወደከተማ ተመልሱ ጠላቶቹን እያፋጠጠ ነው።